(ጥቅምት 19/2017 ዓ.ም) መድረኩ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፣ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ እና በብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም (National ID Ethiopia) አማካኝንት በከተማ አስተዳደሩ የሚገኙ የትምህርት ማህበረሰቡ አካላት የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ እንዲያከናውኑ ለማድረግ እንዲቻል ተካሄዳል::
ዲጂታል መታወቂያ በትምህርት ዘርፉ ያለውን ፋይዳ አስመልክቶ የብሄራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጽ/ቤት አስተባባሪ አቶ ዮዳሄ አርአያስላሴ ምዝገባው የተማሪዎችንና የትምህርት ማህበረሰቡን ማንነትን በመለየት የተማሪን መረጃ በቀላሉ ለማወቅ ያስችላል ብለዋል ::
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ በበኩላቸው ከትምህርት ማህበረሰቡ ጋር በጋራ መስራት ለማህበረሰቡ አቅም ከመሆኑ ጋር በተያያዘ ለስራው ስኬታማነት ጉልበት እንደሚሆን ተናግረዋል ::
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ አዲስ አበባን ዘመናዊ ለማድረግ ለትምህርት ማህበረሰቡ እየተሰጠ ያለውን የኢ-ስኩል ትግበራን ለማሳካት የዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ ማከናወን ለትምህርት ሴክተሩ ትልቅ አቅም የሚፈጥር መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ሀላፊዉ አክለዉም በትምህርት ቤቶች የሚከናወነውን የዲጂታል መታወቂያ ምዝገባ ለማካሄድና አፈፃፀሙን ውጤታማ ለማድግ ሁሉም የትምህርት ማህበረሰቡ አካላት ሀላፊነታቸዉን እንዲወጡ አሳስበዋል፡፡ በተጨማሪም በዲጂታል መታወቂያ የምዝገባ ስርዓት ዘመቻ ውስጥ ከ14 ዓመት በላይ ያሉ ተማሪዎችና በትምህርት መዋቅሩ ውስጥ ያሉ አካላት ሁሉም የዲጂታል መታወቂያ እንዲኖራቸው ለማድረግ እንደሚሰራ ተናግረዋል::
የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ሕግና ፖሊሲ ክፍል ባልደረባ ገብርኤላ አብርሃም የዲጂታል መታወቂያን አስመልክቶ ግንዛቤ ማስጨበጫ ሰነድ አቅርበው በተሳታፊዎች የተነሱ ነጥቦች ላይ ምላሽ ተሰጥቶበታል::
በንቅናቄ መድረኩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የሲቪል ምዝገባ እና የነዋሪነት አገልግሎት ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ አለማየሁ ፣ የብሄራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ጽ/ቤት አስተባባሪ አቶ ዮዳሄ አርአያስላሴ ፣ የሶስቱም ተቋማት ማኔጅመንት አባላት ፣ የኢትዮ ቴሌኮም ሰራተኞች ፣ የክፍለ ከተሞች ትምህርት ፅ/ቤት ሃላፊዎችና አስተባባሪዎች እንዲሁም የሁለተኛ ደረጃ ርዕሳነ መምህራን ተገኝተዋል ::
የትምህርት ማህበረሰቡ የብሔራዊ ዲጂታል መታወቂያ የምዝገባ ንቅናቄ መድረክ ተካሄደ::
0 Comments