አዲስ አበባ፣ ነሀሴ 11 ፣ 2015 ዓ.ም (ትምህርት ቢሮ) በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሁሉም ክፍለ ከተሞች በሚገኙ የ1ኛና 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ላይ እየተካሄዱ የሚገኘው የትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ ሥራዎች ያሉበት ደረጃ ተገመገመ ::
በግምገማው በሁሉም ክፍለከተሞች በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ከሀብት አሰባሰብና የተሰበሰቡ ሀብቶችን ተገቢ ቦታ ላይ ከማዋል አንፃር የተሰሩ ስራዎች እንዲሁም ቀድሞ በእጥረት ይታዩ የነበሩና አሁን በተገኝ ሀብት የተሰጡ መፍትሄዎች ቀርበዋል ::
የትምህርት ቤቶችን መሰረተ ልማት ለማሻሻልና ለትምህርት አሰጣጥ ምቹ ለማድረግ ትምህርት ለትውልድ በሚል ስያሜ የተጀመረውን ንቅናቄ በስኬት ለማጠናቀቅ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት፣ ህብረተሰቡን በማሳተፍ ፣ ከግል ባለሀብትና ግብረሰናይ ድርጅቶች በተገኙ የቁሳቁስና የጉልበትድጋፎች የመማሪያ ክፍሎች ግንባታና እድሳት፤ የምድረ ግቢ ማስዋብና እድሳት እንዲሁም የትምህርት ስራውን ለማገዝ የሚረዱ በርካታ ተግባሮች እየተሰሩ መሆኑ ተብራርቷል ::
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ ወንድሙ ዑመር በሁሉም ክፍለ ከተሞች ያሉ የስራ ሪፖርቶች ይዘት ስራው ትኩረት ተሰጥቶት እየተሰራ መሆኑን እንደሚያመላክት ገልፀዋል :: አቶ ወንድሙ አያይዘውም የንቅናቄ ስራው በሚዲያ እንዲደገፍ የማድረግ ሥራ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ሁሉም ትኩረት እንዲሰጠው አሳስበዋል ::
0 Comments