(ጥቅምት 22/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2017 ዓ.ም የተማሪዎች ፤ መምህራንና መጋቢ እናቶች ደንብ ልብስ ስርጭት አፈጻጸምን በተመለከተ ከመንግስት ግዢ ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ቢሮ እና 18 አቅራቢ ድርጅቶች ጋር ውይይት ተደርጓል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ከደንብ ልብስ አቅራቢዎቹ ጋር ባደረጉት ውይይት ከስርጭት ጋር በተየያዘ የሚጋጥሙ ችግሮች ካሉ ከቢሮው ጋር በመተባበር ወቅቱን ጠብቀው እንዲያከናውኑ አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡
በውይይቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ፤ የመንግስት ግዢና ንብረት ማስወገድ ዋና ዳይሬክተር አቶ መንግስቱ አጥናፉ ፤ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሃላፊ አቶ ወንድሙ ኡመርና የደንብ ልብስ አቅራቢ ድርጅቶች ተገኝተዋል፡፡
የተማሪዎች መምህራንና መጋቢ እናቶች የደንብ ልብስ ስርጭት አፈጻጸምን አስመልክቶ ግምገማ ተካሄደ፡፡
0 Comments