የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ት/ጽ/ቤት የትምህርት ጉባኤ አካሄደ፡፡

by | ዜና

አዲስ አበባ ነሀሴ 27/2015 ዓ.ም  ‘’ሁለንተናዊ ርብርብ ለትምህርት ተቋማት ደረጃ መሻሻል !‘’  በሚል መሪ ቃል የቂርቆስ ክፍለ ከተማ ት/ጽ/ቤት የትምህርት ጉባኤ ያካሄደ ሲሆን በጉባኤው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዘላለም ሙላቱ( ዶ/ር)፣ የቢሮ አማካሪ አቶ ጥላሁን ፍቃዱ ፣ የክፍለ ከተማው ት/ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ በለው ተስፋ ፣ የወረዳ ትምህርት ጽፈት ቤቶች ፣ ርዕሳነ መምህራን ፣ መምህራንና ተማሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

የክፍለ ከተማው ት/ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ በለው ተስፋ በከተማ ደረጃ በተካሄደው 30ኛው የትምህርት ጉባኤ ላይ የክፍለ ከተማው ትምህርት ጽፈት ቤት 1ኛ ሆኖ እውቅና በማግኘቱ ደስተኛ መሆናቸዉን በመግለጽ ለውጤቱ መመዝገብ አስተዋጽዎ ላደረጉ አካላት በሙሉ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

በጉባኤው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዘላለም ሙላቱ( ዶ/ር) ተገኝተው ባስተላለፉት መልዕክት የክፍለ ከተማዉ ትምህርት ጽ/ቤት ላስመዘገበው ውጤት የጉባኤተኛዉ አበርክቶ ያረፈበት በመሆኑ ለውጤቱ መመዝገብ እንኳን ደስ አላችሁ በማለት ለቀጣይ ውጤታማ ስራ መትጋት ይገባል ብለዋል፡፡

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 30
  • 222
  • 1,584
  • 6,364
  • 214,625
  • 214,625