የስርአተ ትምህርት ማበልጸጊያና ትግበራ ዳይሬክቶሬት በአንደኛ ሩብ አመት እቅድ አጻጸም ሪፖርት ዙሪያ ውይይት አካሄደ፡፡

by | ዜና

(ጥቅምት 29/2017 ዓ.ም)በውይይቱ የክፍለ ከተማና ወረዳ ትምህርት ጽህፈት ቤት የስርአተ ትምህርት ትግበራ ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎች የተሳተፉ ሲሆን ከሪፖርቱ ባሻገር የተማሪ መማሪያ መጽሀፍ እና የመምህር መምሪያ ግምገማ ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተካሂዱዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የስርአተ ትምህርት ማበልጸጊያና ትግበራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ታለማ በመርሀ ግብሩ የቢሮውም ሆነ የክፍለከተሞች ከስርአተ ትምህርቱ አተገባበር ጋር በተገናኘ በአንደኛ ሩብ አመት በተከናወኑ ተግባራት ዙሪያ በመወያየት በቀጣይ የተሻለ ስራ ለመስራት ታስቦ መዘጋጀቱን ገልጸዋል፡፡

ዳይሬክተሩ አያይዘውም በአንደኛ ሩብ አመት ከተከናወኑ ተግባራት መካከል ተማሪዎችን በሂሳብና እንግሊዘኛ ትምህርቶች ውጤታማ ለማድረግ የተዘጋጀው ስትራቴጂ ውጤታማ እንዲሆን የድጋፍና ክትትል ስራ መሰራቱ፤የስልጠና ፍላጎት ዳሰሳ በማድረግ ከስርአተ ትምህርቱ አተገባበር ጋር በተገናኘ መምህራንን ጨምሮ ለትምህርት አመራሮችና ባለሙያዎች ስልጠና እንዲሰጥ መደረጉ እንዲሁም በ2017ዓ.ም ተግባራዊ ለሆነው የቅድመ አንደኛ ደረጃ የተዘጋጀው የእንግሊዘኛ ትምህርት ይዘትን መምህራን እንዲተዋወቁ ከመደረጉ ባሻገር የመለማመጃ ደብተሩን እና የማስተማሪያ መጽሀፉ ወደ ማተሚያ ቤት እንዲላክ መደረጉ ከተከናወኑ ተግባራት መካከል እንደሚገኙ አስታውቀዋል፡፡

በመርሀ ግብሩ የቢሮው የስርአተ ትምህርት ማበልጸጊያና ትግበራ ባለሙያ አቶ ፍቃዱ ፋንታዬ በሁሉም የትምህርት አይነቶች የተደረገ የተማሪ መማሪያ መጽሀፍ እና የመምህር መምሪያ የግምገማ ሪፖርት ከማቅረባቸው ባሻገር በክፍለከተማም ሆነ በትምህርት ቤት ደረጃ መጽሀፍ ለመገምገም የሚያግዙ የመገምገሚያ ስልቶችን አቅርበው ውይይት ተካሂዱዋል፡፡

0 Comments