(ህዳር 2/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሰኞ ማለዳ ከስራ ሰዓት መግቢያ በፊት የሚያዘጋጀው የሰራተኞች የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር የተካሄደ ሲሆን በመድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ፣ የቢሮ ማኔጅመንት አባላትና ሰራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል።
በመርሀ ግብሩ ላይ ዶ/ር ቢኒያም አወቀ የቢሮ የአጠቃላይ ትምህርት መረጃ ዝግጅትና አስተዳደር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የስሜት ልህቀትን /Emotional intelligence/ ላይ ያጠነጠነ ሰነድ ያቀረቡ ሲሆን በመድረኩ ማጠቃለያ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ የስሜት ልህቀትን /Emotional intelligence/ ማጎልበት ለውጤታማነት ትልቅ አበርክቶ እንዳለው በማመላከት ይህንን ለማዳበር ራስን ማወቅ ፣ ራስን መቆጣጠር ፣ የሌሎችን ስሜት መረዳት ፣ ተነሳሽ መሆን ፣ አስተውሎትና ማህበራዊ ክህሎትና ማሻሻል መሰረታዊ መሆናቸዉን ገልጸዋል፡፡
የስሜት ልህቀትን /Emotional intelligence/ ማጎልበት ለውጤታማነት ትልቅ አበርክቶ እንዳለው ተገለጸ፡፡
0 Comments