ENGLISH                                                                                                                                                              የዌብሜይል     መልዕክት ይላኩልንየሰዉ ሀብት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት

የሚያከናዉናቸዉ ተግባራት:-

1.የሠው ኃይል ማሟላት

o ቅጥር

o ደረጃ እድገት

o ዝውውር

 • የውስጥ ዝውውር
 • የውጭ ዝውውር

2.የሠራተኞች ድልድል
3.የሠው ኃይል ማስተዳደር፣ማብቃትና ማትጋት

 • ትምህርትና ሥልጠና
 • የሠራተኞች ጥቅማጥቅም
 • ደመወዝ ጭማሪ
 • ልዩ ልዩ ፈቃዶች
 • የዲስኘሊን ጉዳዮች

4.አገልግሎት ማቋረጥ

 • በገዛ ፈቃድ
 • ከሥራ ገበታ በመጥፋት
 • በጡረታ መገለል
 • በሞት


ተገልጋይ ሊያሟላቸው የሚገባ:-

1.የዓመት ፈቃድ ለመጠየቅ፡-

የአመልካች ማመልከቻ ደብዳቤ በሥራ ክፍሉ ኃላፊ /ተወካይ/ እረፍት እንዲወስድ ስለመፈቀዱ የሚገልጽ በጽሁፍ መመራት አለበት፡፡

2.በጡረታ መገለል

የጡረታ መብት አስከባሪ ባለመብት ከሆነ፡-

 • የግል ማመልከቻ ማቅረብ ይኖርበታል
 • ከ18 ዓመት በታች ልጆች ሁለት ጉርድ ፎቶግራፍ
 • የአመልካች 2 ጉርድ ፎቶግራፍ
 • የአመልካች ባል/ሚስት 2 ጉርድ ፎቶ ግራፍ
 • የጋብቻ ማስረጃ ፎቶ ኮፒ

2.1.የጡረታ መብት በውክልና የተሠጠ ግለሰብ የሚፈፀም ከሆነ የሚከተሉትን ቅድመ ሁኔታዎች ማሟላት አለበት፡፡

 • የውክልና ማስረጃ፣
 • የግለሰብ ማመልከቻ፣
 • የባለቤቱና ከ18 ዓመት በታች ያሉ የልጆች ፎቶ ግራፍ እያንዳንዳቸው ሁለት ሁለት ፎቶግራፍ፣
 • የጡረታ መብት የሚከበርበት በውጭ ሀገር የሚኖር ከሆነ የዋናውንና ፖስፖርት ፎቶ ኮፒ፣
 • ባለመብት ከዚህ ዓለም በሞት የተለየ ከሆነ የፍርድ ቤት ማስረጃ ማያያዝ አለበት፡፡