(ጥቅምት 4/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሰኞ ማለዳ ከስራ ሰዓት መግቢያ በፊት የሚያዘጋጀው የሰራተኞች የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር በዛሬው ዕለት የተካሄደ ሲሆን በመድረኩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ፣ የቢሮ ማኔጅመንት አባላትና ሰራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል።
በመርሀ ግብሩ በታሪክ ውስጥ የግለሰቦች አበርክቶ ላይ መሰረት ያደረግ ሰነድ በአቶ ዮሐንስ ተስፋዩ በቢሮ የጥናትና ምርምር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር የቀረበ ሲሆን በመድረኩ ማጠቃለያ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ታሪክን ማወቅ ለነገ ስራ ውጤታማነት አበርክቶ ከፍተኛ መሆኑን በማንሳት ታሪክ በቴክኖሎጂ ታግዞ ሲቀመጥ በቀላሉ ለተደራሹ ለመድረስ ያስችለዋል፡፡
የሰኞ ማለዳ የሰራተኞች የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር ተካሄደ፡፡
0 Comments