የሰኞ ማለዳ የሰራተኞች የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር ተካሄደ፡፡

by | ዜና

(ጥቅምት 18/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሰኞ ማለዳ ከስራ ሰዓት መግቢያ በፊት የሚያዘጋጀው የሰራተኞች የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር በዛሬው ዕለት የተካሄደ ሲሆን በመድረኩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ፣ የቢሮ ማኔጅመንት አባላትና ሰራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል።

በመርሀ ግብሩ በክሪቲካል ቲንኪንግ ላይ መሰረት ያደረግ ሰነድ በአቶ ግሩም አሸናፊ የቀረበ ሲሆን በመድረኩ ማጠቃለያ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ርዕሰ ጉዳዩ መረጃዎችን መሰረት በማድረግ ነገሮችን የምናይበትንና የምንተነትንበትን መንገድ በክሪቲካሊ ቲንኪንግ (በቅጥነተ ህሊና) ቅኝት ውስጥ እንዲያልፍ እና ለምንሰጣቸዉም ውሳኔዎች ሚዛናዊነት እንዲኖር ያግዛል ብለዋል፡፡ ሀላፊው አክለዉም ክሪቲካል ቲንኪንግ የራሳችንን አስተሳሰብ እንድንይዝና ያመንበትን እንድንናገር የሚያግዝ በመሆኑ የሁል ጊዜ ተግባራችን አድርገን መውሰድ ተገቢ እንደሆን ተቁመዋል፡፡

0 Comments