የሰኞ ማለዳ የሰራተኞች የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር ተካሄደ፡፡

by | ዜና

(ታህሳስ 28/2017 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሰኞ ማለዳ ከስራ ሰዓት መግቢያ በፊት የሚያዘጋጀው የሰራተኞች የዕውቀት ሽግግር መርሀ ግብር የተካሄደ ሲሆን በመድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ፣ ማኔጅመንት አባላትና የትምህርት ቢሮ ሰራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል።

               
በመርሀ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ትምህርት ፈተና እና ምዘና ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ተሾመ ደገፋ ያስተሳሰብ ለውጥ ለግል እድገት በሚል ርዕሰ ጉዳይ ላይ እውቀታቸውን ያካፈሉ ሲሆን በመድረኩ ማጠቃለያ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ መድረኩ የእውቀት ሽግግሮች እንዲጎለብቱ ትልቅ ምህዳር እየሆነ መምጣቱን ጠቅሰው የቀረበው ርዕሰ ጉዳይ ለስራ አለም ብቻ ሳይሆን ለሰራተኞች የግል ህይወትም ትልቅ አበርክቶ ይኖረዋል ብለዋል፡፡

0 Comments