የሰራተኞች የዕውቀት ሽግግር መርሃ ግብር ተካሄደ፡፡

by | ዜና

(ቀን ሚያዚያ 4/ 2016 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሚያዘጋጀው የሰራተኞች የጋር መዓድ መቋደስና የዕውቀት ሽግግር መርሃ ግብር በዛሬው እልት የተካሄደ ሲሆን በመድረኩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ማኔጅመንት አባላትና ሰራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል።

በመርሀ ግብሩ  ላይ የትምህርት ስራዎች አማካሪ በሆኑት በአቶ ሳሙኤል መንገሻ በዴሊቨሮሎጂ ላይ ሰነድ ቀርቦ ውይይት ተካሄዶበታል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ  የሆኑት አቶ አሊ ከማል በመርሀ ግብሩ ማጠቃለያ ባስተላለፉት መልዕክት የዕውቀት ሽግግር መድረኩ በርካታ እውቀቶች የሚቀሰሙበት ፣ ለበለጠ ስራ የሚያነሳሱ የህይወት ተሞክሮች የሚገኙነት የጎለበት መድረክ በመሆን እያገለገለ መሆኑን በመጥቀስ  ለወጤታማነቱ በትኩረት መስራት ይገባል ብለዋል፡፡

0 Comments

SITE VISITORS

  • 1
  • 187
  • 249
  • 2,423
  • 8,975
  • 243,957
  • 243,957