የሰራተኞች የዕውቀት ሽግግር መርሃ ግብር ተካሄደ፡፡

by | ዜና

(ግንቦት 5 ቀን 2016 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከስራ ሰሃት መግቢይ በፊት የሚያዘጋጀው የሰራተኞች የዕውቀት ሽግግር መርሃ ግብር በዛሬው ዕለት የተካሄደ ሲሆን በመድረኩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ፣ የቢሮ ማኔጅመንት አባላትና ሰራተኞች ተሳታፊ ሆነዋል።

በመርሀ ግብሩ  ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ሱፕርቪዥን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጸጋዩ አሰፋ ትምህርትና ለውጥ በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ሰነድ አቅርበው ውይይት ተካሄዶበታል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ  ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ በማጠቃለያ መልዕክታቸው የስራ ውጤታማነት ሊመዘገብ የሚችለውና የታለመውን አላማ ከግብ ማድረስ የሚቻለው ተከታታይነት ያለው ለውጥ እንዲመጣ በትኩረት በመስራትና በጋራ በመሰናሰል በመስራት በመሆኑ ሰራተኛው ለዚህ ትኩረት መስጠት ይጠበቅበታል ብለዋል፡፡

 

0 Comments

SITE VISITORS

  • 0
  • 187
  • 249
  • 2,423
  • 8,975
  • 243,957
  • 243,957