የሪሜዲያል ፕሮግራም ተማሪዎች ፈተና ማጠናቀቂያ ጊዜ ተገለፀ።

በ2014ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ወስደው በልዩ ሁኔታ በሪሜዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ የሆኑ  ተማሪዎች ፈተናና ተዘጋጅቶ እንዲላክና አጠቃላይ ሂደቱ  እስከ ሰኔ 30/2015ዓ.ም ድረስ እንዲጠናቀቅ በትምህርት ሚኒስቴር አቅጣጫ ተቀምጧል።

ፈተናውም በዩኒቨርሲቲ ቆይታቸው በተሰጠው ትምህርት መሠረት ከማዕከል በጋራ ተዘጋጅቶ ለተቋማት እንዲላክ  ተብሏል ።

በዚህም መሰረት በሴሚስተሩ በተሰጠው ትምህርት የተቋማት የውስጥ ፈተና ውጤት 50 ከመቶ እንዲሁም በማዕከል የተዘጋጀው ፈተና ውጤት 50 ከመቶ  ይይዛል ተብሏል።

ተማሪዎችም በ2016 ዓ.ም ትምህርታቸውን ለመከታተል ብቁ ሆነው ለመገኘት የሁለቱ ድምር አማካይ 50 ከመቶና በላይ ውጤት ማስመዝገብ ይጠበቅባቸዋልም ተብሏል።

ዩኒቨርሲቲዎችም ፈተናውን በማስተዳደርና ውጤት በመግለጽ በ2016 የፍሬሽማን ፕሮግራም ለመከታተል ብቁ የሆኑ ተማሪዎችን  ለይተው እስከ ሰኔ 30/2015ዓም እንዲያጠናቅቁ ተገልጿል።

ዩኒቨርሲቲዎች ያላቸውን ስራ በማጠናቀቅ የ2016 የትምህርት ካሌንደር የተስተካከለ እንዲሆን ኃላፊነታቸውን እንዲወጡ  ሚኒስቴሩ አሳስቧል።

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 0
  • 175
  • 2,114
  • 9,135
  • 234,185
  • 234,185