የማለዳ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ለንቁ አዕምሮ በሚል መሪ ቃል በትምህርት ቤቶች የሚካሄደው ስፖርታዊ እንቅስቃሴ በዛሬው እለትም ቀጥሎ ተካሂዷል።

by | ዜና

(ጥቅምት 27/2016 ዓ.ም)  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱን ጨምሮ የቢሮው ማኔጅመንት አባላትና የአራዳ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ ደረሰ በተገ ኙበት በዳግማዊ ሚኒሊክ 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከተማሪዎች ጋር የተለያዩ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ተካሂደዋል።

የማለዳ ስፖርት በአዕምሮ የበለጸገና በአካል የዳበረ ትውልድ በመፍጠር ተማሪዎች በትምህርታቸው ውጤታማ እንዲሆኑ የሚያስችል መርሀ ግብር በመሆኑ ፕሮግራሙ ከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች በሳምንት ሁለት ቀን ተግባራዊ እየሆነ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ አ ታውቀዋል።

የአራዳ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሀብታሙ ደረ ሰ በበኩላቸው በትምህርት ቤቶች የሚካሄድ የማለዳ ስፖርት እንቅስቃሴ ተማሪዎች ተነቃቅተው ወደ መማሪያ ክፍል እንዲገቡ የሚያስችል ተግባር በመሆኑ ፕሮግራሙ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አስረድተዋል።

ተማሪዎች ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን በመስራት በአካልም ሆነ ስነልቦና ዝግጁ ሆነው በትምህርታቸው ውጤታማ መሆን እንደሚገባቸው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሲ ሳይ እንዳለ ገልጸዋል።

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 178
  • 249
  • 2,414
  • 8,966
  • 243,948
  • 243,948