የማለዳ ስፖርታዊ እንቅስቃሴ ለንቁ በአካልና በአዕምሮ የዳበረ ትውልድ ለሀገር እድገት! በሚል መሪ ቃል በትምህርት ቤቶች የሚካሄደው ስፖርታዊ እንቅስቃሴ በዛሬው እለትም ተካሂዷል።

by | ዜና

(አዲስ አበባ ህዳር 27/2016 ዓ.ም )  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ማኔጅመንት አባላትና የልደታ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ  እጅጋየሁ አድማሱ በተገኙበት በተስፋ ኮከብ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት   ከተማሪዎች ጋር የተለያዩ ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች ተካሂደዋል።

የማለዳ ስፖርት በአካልና በአዕምሮ  የዳበረ ትውልድ በመፍጠር ተማሪዎች በትምህርታቸው ውጤታማ እንዲሆኑ የሚያስችል መርሀ ግብር በመሆኑ ፕሮግራሙ ከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች በየሳምንቱ ተግባራዊ እየሆነ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ  ጵፈት ቤት ኃላፊ አቶ ሲሳይ እንዳለ  አስታውቀዋል።

የልደታ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ  እጅጋየሁ አድማሱ በበኩላቸው በትምህርት ቤቶች የሚካሄድ የማለዳ ስፖርት እንቅስቃሴ በክፍለ ከተማው በየሳምንቱ እንደሚከናወን ጠቅሰው ተማሪዎች ተነቃቅተው ወደ መማሪያ ክፍል እንዲገቡ የሚያስችል ተግባር በመሆኑ ፕሮግራሙ ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ አስረድተዋል።

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 30
  • 222
  • 1,584
  • 6,364
  • 214,625
  • 214,625