(ቀን 4/2/2016 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ለ2016 የትምህርት ዘመን አገልግሎት የሚውሉ የመማሪያ መጻሕፍት ስርጭት በማካሄድ ላይ ይገኛል።
ለትምህርት ዘመኑ አስፈላጊ የሆኑ በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት መስረት በአዲስ አበበ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የታተሙ የሁሉም የትምህርት አይነቶች የአንደኛ ደረጃ ትምህርት የተማሪ መማሪያ መጻሕፍትና የመምህሩ መምሪያዎች በሚኒሊክ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እንዲሰራጭ በመደረግ ላይ መሆኑን የአዲስ አበበ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊ አቶ ወንድሙ ዑመር ገልፀዋል፡፡
አቶ ወንድሙ አክለውም የግል ትምህርት ተቋማት ሚኒሊክ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በመምጣት የመማሪያ መጻሕፍትንና የመምህር መምሪያን መውሰድ የሚችሉ መሆኑን ያሳወቁ ሲሆን የግል ትምህርት ተቋማት በሚመጡበት ጊዜ ከዚህ ቀደም ለክፍለ ከተማ ት/ጽ/ቤት ያስገቡትን የፍላጎት ዝርዝር በመያዝና በክፍለ ከተማው ት/ጽ/ቤት ማህተም በማረጋገጥ ሊሆን ይገባል ብለዋል፡፡
0 Comments