ENGLISH                                                                                                                                                              የዌብሜይል     መልዕክት ይላኩልንየለዉጥ ስራ አመራርና አፈፃፀም ክትትልና ምዘና ቡድን

መግቢያ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የትምህርት ስርዓቱ ውስጥ ቁልፍና ልዩ ትኩረት የሰጣቸውን ውጤታማ የትምህርት አገልግሎት መስጠትና  የማስፈጸም አቅም ግንባታ ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ከፍተኛ ርብርብ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ ይህም በከተማ አስተዳደሩ ፈጣን ቀልጣፋና ውጤታማ አገልግሎት ለመስጠት የአጠቃላይ ትምህርት ጥራት ፓኬጅ ፕሮግራሞችን ተግባራዊ በማድረግና የለውጥ መሣሪያዎችን (ሪፎርም) አቀናጅቶ በመጠቀም ውጤታማ ስራዎች ተሰርተዋል፡፡ በተለይ መሰረታዊ የስራ ሂደት ለውጥ ጥናትና ሚዛናዊ የስራ አመራርና የውጤት ምዘና ስርዓትን በትምህርት ሴክተሩ በየደረጃው ባሉት ስራ ሂደቶች ፣ ክ/ከተማ፣ ወረዳና ት/ቤቶች በመተግበር ውጤታማ ስራ እየተሰረ መሆኑን የታቀደ ክትትልና ድጋፍ ይደረጋል፡፡

ስራ ሂደቱ የለውጥ መሳሪዎችን (BPR እና BSC)ትግበራ በመከታተል፣ በመደገፍና የአፈፃፀም ውጤታቸውን በመመዘን የላቀ ውጤት ያመጡት የትምህርት ተቋማት የሚበረታቱበት ዝቅተኛ ውጤት ያመጡትን በማብቃትና በመደገፍ ወደሚፈለገው የለውጥ ጐዳና እንዲገቡ አሠራር ለመዘርጋት በርካታ ስራዎችን አከናውኗል፡፡

የስራ ሂደቱ ዓላማ

የክትትል፣ድጋፍና ግምገማ ሥርዓትን በመዘርጋት፡-

 • ስትራቴጂ ተኮር የሆኑ ተቋማትን መፍጠር፣
 • ተቋማዊ ሽግግርን ማረጋገጥ
 • ግልጽነትና ተጠያቂነትን በየደረጃው በማስፈን የህብረተሠቡን ተጠቃሚነት ማረጋገጥ ፡፡

ስራ ሂደቱ  የሚሰጡ አገልግሎቶች፡-

 • የBSC (ስኮር-ካርድ) ማዘጋጀትና ለየትምህርት ተቋሙ ማድረስ
 • የለውጥ ስራ አፈጻጸም ክትትልና ድጋፍ ማድረግ
 • ክትትልና ድጋፍ ለተደረገባቸው የትምህርት ተቋማት  ግብረ-መልስ መስጠት
 • በለውጥ መሣሪያዎች ዙሪያ ስልጠና መስጠት
 • የትምህርት ተቋማት ስራ አፈጻጸም  መመዘን
 • በምዘነው መሠረት ደረጃ መስጠት
 • ምርጥ ተሞክሮ መለየትና እንድቀመር ማመቻቸት
 • የማስፋ ስትራቴጂን ትግባራ የውይይት መድረኮችን ማዘጋጀት

የልምድ ልውውጥና ማስፋት ስትራቴጂ እንቅስቃሴ

 •   ሞዴል ት/ቤቶችን በማብቃት በበጀት ዓመቱ የልምድ ልውውጥ  ተደርጓል
 •  ቁጥራቸው አንድ ሺ የሚሆኑ የት/ተቋማት አመራሮችና ባለሙያዎች የተሳተፉበት ከተማ አቀፍ የምርጥ ተሞክሮ ውይይት መድረክ ተከሄዷል፡፡
 • አምስት ምርጥ ተሞክሮዎች ተቀምረው እንድስፋፉ ተደርጓል፡፡
 • ለትምህርት ተቋማት አመራሮች፣ባለሙያዎችና ሱፐርቫይዘሮች  በምርጥ ተሞክሮ መቀመርና ማስፋፈት ላይ ሥልጣና ተሰጥቷል፡፡

የትምህርት ተቋማት የስራ አፈጻጸም ምዘና ስራ

የትምህርት ተቋማት በርካታ ከመሆናቸው አንጻር የሁሉንም ስራ አፈጻጸም መመዘን ከባድ ቢሆንም  መዛኝ ባለሙያዎችን ከወረዳዎች ጭምር በመመልመል ስለምዘናው ኦሬንቴሽን በመስጠት በሁሉም ት/ተቋማት ምዘና የተከሄደ ሲሆን የአፈጻጸም ደረጃም ተሠጥቷል፡፡

የትምህርት ሴክተሩን  ስኬታማ ለማድረግ ከአመራሩና ከፈፃሚው ምን ይጠበቃል ?

 1. ከአመራሩ ምን ይጠበቃል ?
 • በዕውቀት እና  በእምነት መምራት ፣
 • ለውጥን የሚያደናቅፍ ማንኛውንም አፍራሽ የሆነ ሐሳብ በፅናትና በግንባር ቀደምትነት መታገል ፣
 • የለውጥ ኮሚኒኬሽን ስራ በበላይነት መምራት ፣
 • ግልፅና ተጠያቂነት ያለው አሰራር እንዲተገበር ማድረግ ፣
 • በባላንስ ስኮር ካርድ ትግበራ የተገኙት ምርጥ ተሞክሮዎችን ተቀምረው እንዲስፋፉ ማመቻቸት
 • በተግባር የተገለፀ አርአያነትና ቁርጠኝነት ማሳየት፣
 • ስትራቴጂክ ግቦች ወደ ትግበራ ለመለወጥ ውስጣዊና ውጫዊ  ትስስር  እንዲፈጠር ማመቻቸት፣
 • አጠቃላይ ኘሮግራሙን ለመፈፀም የሚያስፈልግ ግብዓት (የሰው ሀይል፣ በጀትና ማቴሪያል)መመደብ ፣
 • የተጓዳኝ አደረጃጀትና ሌሎችም አደረጃጀቶችን በመጠቀም የውይይቱ አጀንዳ በለውጥ መሣሪያዎች ላይ ትኩረት እንዲሰጥበት ማድረግ፣
 1. ከፈፃሚ ምን ይጠበቃል ?
 • በችሎታ፣ክህሎትና አመለካከት የራስን ብቃት በማሻሻል ንቁ ተሳትፎ ማድረግ ፣
 • ለውጤትና ውጤታማነት መስራት  የሴክተሩ ባህል ማድረግ ፣
 • ለውጤታማና ስኬታማ አፈፃፀም መትጋት
 • የዕለት ተዕለት ስራን ስትራቴጂካዊ ማድረግ
 • ለላቀ ውጤት መስራት ፣
 • የአፈፃፀም ውጤቶች በመረጃዎች መደገፍና መረጃዎችን ታአማኒነት ማድረግ ፣
 • የየቀን ስራ ከሚዛናዊ ስራ አመራርና ውጤት ምዘና ስርዓት  ግቦች አንፃር መቃኘት ፣
 • ለተግባራት መሳካት የእርስ በእርስ መማማር ዘይቤን ማሳደግ ፣
 • የየዕለቱ ተግባራት የሚለኩት በተቀመጠው እስትራቴጂክ ግቦች ከማሳካትና አስትዋፅኦ /Value add / በሚያደርግ መሰረት ማከናወን
 • ስኬት የሁሉም ሰራተኞች ክንውን ድምር ውጤት መሆኑን መረዳትና
 • የኔ ስራ ለሴክተሩ ስኬት ምን ያህል አስተዋፅኦ እያደረገ ነው በሚል መንፈስ መስራት የሚሉተን ያጠቃልላል፡፡