የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተናን ማስጀመሩን አሳወቀ፡፡

by | ዜና

ቀን 27/10/2014 ዓ.ም

የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተናን ማስጀመሩን አሳወቀ፡፡

የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት በዛሬው እለት የከተማ አቀፍ የ8ኛ ክፍል ፈተና በክፍለ ከተማው ባሉ በሁሉም የመንግስት እና የግል የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ተቋማት ፈተናውን መስጠት መጀመሩን ገልጿል።

በክፍለ ከተማዉ የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና በክፍለ ከተማ በሚገኙ አስራ ሥስት የመፈተኛ ጣቢዎች 7,404 ተማሪዎች ፈተናውን በዚህ ቀን መውሰድ መጀመራቸውንም ጨምሮ አሳውቋል።

በአሁን ሠዓት ፈተናው ፍፁም ሠላማዊ በሆነ መልኩ ተማሪዎቹ በተረጋጋ መንፈስ ፈተናውን መውሰድ መጀመራቸውን የትምህርት ጽ/ቤት የገለፀ ሲሆን ፈተናው ለሥስት ተከታታይ ቀናትም እንደሚቆይ ተጠቁሟል።

የ8ኛ ክፍል የከተማ አቀፍ ፈተናው ያስጀመሩት የለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ትምህርት ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ባዩማ ወርቁ ለተማሪዎቹ ባስተላለፉት መልዕክት እናንተ የዛሬ ተማሪ የነገ የሀገር የተስፋ ብርሀን ናቹ ስለዚህ ትልቅ ራዕይ ሰንቃቹ የተሻለች እና ለሁሉ የምትሆን ሀገር በእናንተ ጊዜ እውን እድትሆን ይኸው ጉዞውን ዛሬ ጀምራቹዋል በማለት ለተማሪዎች መልካም ውጤትን ተመኝተዋል።

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 187
  • 249
  • 2,423
  • 8,975
  • 243,957
  • 243,957