የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች ስፓርታዊ ውድድር ከግንቦት 10 እስከ 24/2016 ዓ/ም ድረስ እንደሚካሄድ ተገለጸ፡፡

by | ዜና

(ግንቦት 6 ቀን 2016 ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮና የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ  በጋራ በመሆን ከግንቦት 10/2016 ዓ/ም ጀምሮ የሚካሄደውን የሁለተኛ ደረጃ  ትምህርት  ቤቶች  የተማሪዎች ስፓርታዊ  ውድድርን አስመልክተው  ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡

በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፓርት ቢሮ ሀላፊ አቶ በላይ ደጀን ፣ የሁለቱም ተቋማት ማኔጅመንት አባላት ፣ የሁለቱም ተቋማት የክፍለ ከተማ ት/ጽ/ቤት ሀላፊዎችና ጋዜጠኞች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ  ስፖርታዊ ውድድሩ በአዕምሮአቸዉና በአካላቸዉ ብቁ የሆኑ ዜጎችንና ተተኪ ስፖርተኞችን ለማፍራት ያግዛል ያሉ ሲሆን በሁለቱ ተቋማት መካከል በተፈጠሩ የስራ ትስስሮች በርካታ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸዉን በመግለጽ ከግንቦት 10 እስከ 24/ 2016 ዓ.ም ደረስ የሚካሄደዉ ስፖርታዊ ውድድር የዚህ አንዱ መሳያ ነዉ ብለዋል፡፡

ሀላፊዉ አክለዉም ስፖርታዊ ውድድሩ “የትምህርት ቤቶች  ስፖርታዊ ውድድር ለሰላም ፣ ለአብሮነትና ለሁለንተናዊ ብልጽግና!” በሚል መሪ ሀሳብ እንደሚካሄድ በመግለጽ ለስኬታማነቱ በየደረጃዉ የሚገኙ የሁለቱም ተቋማት አመራሮችና ባለሙያዎች ርብርብ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው አሳስበዋል፡፡ ስፖርታዊ ውድድሩም በከተማው ውስጥ ያሉትን ተማሪዎች በማቀራረብ የተጠናከረ የወዳጅነትና የወንድማማችንት መንፈስ እንዲጠናከር  የሚያስችል የስፖርት ንቅናቄ  መሆኑን ጨምረዉ አሳውቀዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ደጀን በላይ በበኩላቸው ውድድሩ በስድስት የስፓርት ዓይነቶች የሚካሄድ መሆኑን በመግለጽ ከ18ሺ በላይ ተማሪዎች በውድድሩ ላይ ይሳተፋሉ ብለዋል፡፡ ከ11ዱም ክፍለ ከተማዎች የ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ትምህርት ቤታቸውን ወክለው በአትሌቲክስ ፣ በእግር ኳስ ፣ በቮሊቦል ፣ በእጅ ኳስ፣ በቅርጫትና  በጠረጴዛ ቴኒስ  በሁለቱም ጾታ ፉክክር እንደሚደረግ ጨምረዉ ገልጸዋል፡፡

0 Comments

SITE VISITORS

  • 0
  • 178
  • 249
  • 2,414
  • 8,966
  • 243,948
  • 243,948