ዘንድሮ ለ18ኛ ጊዜ ‘’ብዝኃነትና እኩልነት ለሀገራዊ አንድነት!’’ በሚል መሪቃል የሚከበረውን የብሄሮች ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ቀንን በአል ምክንያት በማድረግ በየደረጃው ስልጠና ለሚሰጡ አሰልጣኞች ስልጠና ተሰጠ፡፡

by | ዜና

(ህዳር 7 ቀን 2016 ዓ.ም) በመርሀ-ግብሩ ከክፍለከተማና ወረዳ ትምህርት ጽህፈት ቤቶች የተውጣጡ ተወካዮች ተሳታፊ የሆኑ ሲሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሱፐርቫይዘር የሆኑት አቶ ዘሪሁን አለማየሁ ሕብረብሄራዊና ፌደራሊዝም ስርአት ለሰላም ግንባታ በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ስልጠና ሰተው ተሳታፊዎች ውይይት አካሂደዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አማካሪ አቶ ጥላሁን ፍቃዱ በውይይቱ መክፈቻ ባስተላለፉት መልዕክት የብሄሮች ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ቀን ኢትትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ ብሄረሰቦች ማንነታቸው እውቅና ያገኘበት ከመሆኑ ባሻገር ራስን በራስ የማስተዳደር ጥያቄዎቻቸው የተመለሰበት እንደመሆኑ የፓናል ውይይቱ ተሳታፊዎች በስልጠናው በቂ ግንዛቤ በመያዝ በየደረጃው ለሚገኙ የትምህርት ባለድርሻ አካላት እውነታውን መሰረት ያደረገ ስልጠና መስጠት እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል፡፡

የዘንድሮው የብሄሮች ብሄረሰቦችና ሕዝቦች በአል በከተማ አስተዳደሩ ከትምህርት ቤት ጀምሮ እስከ ማዕከል ድረስ በፓናል ውይይቶች ፣ ባህላዊ ፌስቲቫሎችና በተማሪዎች መካከል በሚካሄድ ህገመንግስትን እና የፌደራል ስርአቱን መሰረት ባደረገ የጥያቄና መልስ ውድድር በድምቀት እንደሚከበር  የቢሮ  ሀላፊ አማካሪ ወ/ሮ አበበች ነጋሽ በመርሀ ግብሩ ላይ ገልጸዋል፡፡

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 205
  • 158
  • 7,078
  • 31,331
  • 147,475
  • 147,475