ዘንድሮ ለ18ኛ ጊዜ ብዝኃነትና እኩልነት ለሀገራዊ አንድነት! በሚል መሪ ቃል የሚከበረውን የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ቀን ምክንያት በማድረግ በተማሪዎች መካከል ሲካሄድ የቆየው ከተማ አቀፍ የጥያቄና መልስ ውድድር ተጠናቀቀ።

by | ዜና

(ህዳር 20 ቀን 2016 ዓ.ም)  በዛሬው የማጠቃለያ ውድድር ቀደም ሲል ከትምህርት ቤት ጀምሮ በወረዳ ፣ ክፍለ ከተማና ከተማ ደረጃ በተካሄደ ውድድር አሸናፊ የሆኑ አምስት ከአማርኛ አምስት ከአፋን ኦሮሞ በድምሩ 10 የሰባተኛ እና ስምንተኛ ክፍል ተማሪዎች የተሳተፉ  ሲሆን ውድድሩም በዋናነት ህገ-መንግስትና የፌደራሊዝም ስርዓትን መሰረት አድርገው  በተዘጋጁ ጥያውቄዎች ላይ መሰረት በማድረግ ነው የተካሄደው ።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በማጠቃለያ ውድድሩ መክፈቻ ባስተላለፉት መልዕክት 18ኛውን የብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን ምክንያት አድርጎ  በተማሪዎች መካከል የሚካሄድ የጥያቄና መልስ ውድድር  ተማሪዎች ከህገ-መንግስትም ሆነ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት ጋር በተገናኘ በስርዓተ ትምህርቱ የተካተቱ ይዘቶችን በአግባቡ እንዲረዱ ከማስቻሉ ባሻገር በሀገራቸው ስላሉ  ህዝቦች ባህልና ወግ በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸው የሚያስችል መርሀ – ግብር መሆኑን  ገልጸው የጥያቄና መልስ ውድድሩ ከትምህርት ቤት ጀምሮ እስከ ከተማ ድረስ በስኬት እንዲካሄድ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የትምህርት አመራሮች ፣ባለሙያዎችና መምህራን ምስጋና አቅርበዋል ።

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የማዘጋጃ ቤታዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ስብሳቢ አቶ ማሾ ኦላና በበኩላቸው የብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን በሀገራችን ህብረ ብሔራዊ ፌደራላዊ ስርአዓት እውን መሆኑን ተከትሎ የሚከበር በአል እንደሆነ ጠቁመው እለቱን አስመልክቶ በተማሪዎች የሚካሄድ የጥያቄና መልስ ውድድር ተማሪዎቻችን ከህብረ ብሔራዊ ፌደራላዊ ስርዓት ጋር በተገናኘ ያላቸውን ግንዛቤ የሚያሳድግ መሆኑን ገልጸዋል።

በከተማአቀፉ የማጠቃለያ  የጥያቄና መልስ ውድድር ተማሪ ሱመያ አልዩ ከጉለሌ ክፍለ ከተማ ፣ አሮን ሚፍታ ከለሚ ኩራ፣ ኤዶም መኮንን ከንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በአማርኛ ዘርፍ ከ1ኛ እስከ 3ኛ በመውጣት ሲያሸንፉ በተመሳሳይ  ተማሪ አብዲ ታምሩ ከጉለሌ ክፍለ ከተማ፣ተማሪ ኪያ ፉፋ ከንፋስ ስልክ ላፍቶ እንዲሁም ተማሪ ኬና ወንድሙ ከአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በአፋን ኦሮሞ ዘርፍ ከ1ኛ እስከ 3ኛ በመውጣት ከእለቱ የክብር እንግዶች የተለያዩ ሽልማቶች ተበርክቶላቸዋል።

 

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 28
  • 222
  • 1,582
  • 6,362
  • 214,623
  • 214,623