ከተማ አቀፍ የተማሪዎች የማለዳ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማስጀመሪያ መርሀ-ግብር ተካሄደ።

by | ዜና

(ጥቅምት 14/2016 ዓ.ም) በጉለሌ ክፍለ ከተማ በሚገኘው እቴጌ መነን የሴት ተማሪዎች ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ፣ የቢሮ ማኔጅመንት አባላት ፣ የአዳሪ ትምህርት ቤቱ ተማሪዎች ፣ መምህራንና ርዕሳነ መምህራን በተገኙበት ከተማ አቀፍ የተማሪዎች የማለዳ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማስጀመሪያ መርሀ-ግብር ተካሄደ።

በመድረኩ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ  የ2016 የትምህርት ዘመን ከተማ አቀፍ የተማሪዎች የማለዳ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማስጀመሪያ መርሀ-ግብር መጀመሩን በመግለፅ ከሁለት አመታት በፊት የተጀመረው የማለዳ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ዘንድሮ በአዕምሮና በአካል የዳበረ ትውልድ ለሀገር እድገትና  ብልጽግና! በሚል መሪ ሀሳብ የማለዳ እስፖርታዊ እንቅስቃሴ በሁሉም ትምህርት ቤቶች የኢትዮጵያ ህዝብ መዝሙር ከመዘመሩ በፊት  ይካሄዳል ብለዋል፡፡

ሀላፊው አክለውም በትምህርት ቤቶች የሚደረገው የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በአዕምሮዋቸው የነቁና በአካላቸው የዳበሩ ሁለንተናዊ ስብዕና የተላበሱ ዜጎችን እንዲኖሩ ለማድረግ ያለመ ነው ብለዋል።

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 0
  • 175
  • 2,114
  • 9,135
  • 234,185
  • 234,185