ከተማ አቀፍ የመምህራን ስፖርታዊ ውድድር በመጪው ቅዳሜ በድምቀት እንደሚጀመር ተገለጸ።

ለውድድሩ እስካሁን እየተደረገ የሚገኘውን የቅድመ ዝግጅት ስራ በተመለከተ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ እና የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ አመራሮች ከክፍለ ከተማ ጽህፈት ቤት ኃላፊዎችና ከአዲስ አበባ መምህራን ማህበር ስራ አስፈጻሚዎች ጋር ውይይት አካሂደዋል።

በመምህራን መካከል የሚካሄድ የስፖርት ውድድር የርስ በእርስ ትውውቅን ከማጠናከሩ ባሻገር በትምህርት ሴክተሩ የሚካሄዱ ስፖርታዊ ውድድሮች ቀጣይነት እንዲኖራቸው የሚያስችል ተግባር መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ገልጸው ዘንድሮ የሚካሄደው የመምህራን ስፖርታዊ ውድድር በድምቀት ተጀምሮ እንዲጠናቀቅ በየደረጃው ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት ማድረግ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የአዲስ አበባ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ ዳዊት ትርፉ በበኩላቸው ውድድሩ ከመጪው ቅዳሜ ጀምሮ ከሁሉም ክፍለ ከተሞች በተውጣጡ መምህራን መካከል በተለያዩ የስፖርት ማዘውተሪያ ስፍራዎች እንደሚካሄድ ጠቁመው ውድድሩም በእግር ኳስ፣ቮሊቦል እና ጠረጴዛ ቴኒስ በሁለቱም ጾታዎች እንደሚካሄድ አስታውቀዋል።

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 183
  • 249
  • 2,419
  • 8,971
  • 243,953
  • 243,953