ከሱማሌ ክልል ትምህርት ቢሮ የመጡ የትምህርት አመራሮች ቦሌ ክፍለከተማ የሚገኘውን አልፋ መስማት የተሳናቸው ልዩ የቅድመ 1ኛ እና 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤትን ጎበኙ።

by | ዜና

(ቀን 7/2/2016 ዓ.ም)  አልፋ መስማት የተሳናቸው ልዩ ቅድመ አንደኛ እና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በ2016ዓ.ም የትምህርት አመት 66 ወንድና 59 ሴት በድምሩ 125 መስማት የተሳናቸውን ተማሪዎች ተቀብሎ በማስተማር ላይ እንደሚገኝ የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር አቶ ሞላ ውሌ በጉብኝቱ ወቅት አስታውቀዋል።

ርዕሰ መምህሩ አክለውም በትምህርት ቤቱ የምልክት ቋንቋ የሚችሉ 34 መምህራን ተመድበው በማስተማር ላይ እንደሚገኙ ገልጸው ትምህርት ቤቱ በከተማ አስተዳደሩ የሚገኙ ሌሎች ትምህርት ቤቶች የሚተገብሩትን ስርአተ ትምህርት እንደሚጠቀም አስገንዝበዋል።

የጉብኝቱ ተሳታፊዎችን በትምህርት ቤቱ መስማት ለተሳናቸው ተማሪዎች እየተደረገ የሚገኘው ድጋፍ በክልላቸው ለመክፈት  ላሰቡት ተመሳሳይ ትምህርት ቤት ተሞክሮ የወሰዱበት የልምድ ልውውጥ መርሀ ግብር መሆኑን ገልጸዋል።

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 205
  • 158
  • 7,078
  • 31,331
  • 147,475
  • 147,475