አዲስ ዓመት አዲስ ተስፋን እና ትጋትን የሚያላብስ የአዲስ ነገር መጀመሪያ እንደመሆኑ መጠን ከወዳጅ ከዘመድ ጋር እንኳን ከዘመን ዘመን አሽጋገራችሁ ተባብለን ፤ በደስታ የምንቀበለው ከአስራ ሶስት ወራት በሀላ የሚመጣ ልዩ መገለጫ ቀን ነው፡፡
አዲስ ዓመት ከአዲስ ህልምን ለማሳካት ከምናስቀምጠው እቅድ ጋር እጅጉኑ የተቆራኘ ነው፡፡ በመሆኑም በአዲስ ዓመት ልናካውናቸው ያስቀመጥናቸውን እቅዶቻችንን ለማሳካት የሚቻለን ካለፈው አፈጻጸማችን መነሳት ስንችል መሆኑን መዘንጋት ተገቢ አይድለም፡፡
የ2015 የትምህርት ዘመን ያሰመዘገብናቸውን የላቁ የትምህርት ስራዎች አፈጻጸሞን በተሻለ ትግበራ ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስም ሆነ እጥረቶቻችንን ለማረም የምንችለው የሚናችን መወጣት ስንችል ነው፡፡
ከዚህም ጎን ለጎን በ2015 የትምህርት ዘመንም በትምህርት ዘርፍ ስራችን ተጨባጭ ተግባራት ለማከናወን ችለናል፡፡ ይህ እንዲሆን የተማሪዎች ፣ የመምህራን ፣ የትምህርት ባለድርሻ አካላት እና የትምህርት አመራሮች ሚና የጎላ በመሆኑ ምስጋና ላቀርብ እወዳለሁ፡፡
ለሀገር እንዲሁም ለትምህርት ተቋማት ሰላም እና መረጋጋት የትምህርት ማህበረሰቡ አካላት ከዚህ ቀደም ስታደርጉት የነበረውን አስተዋጽዎ በአዲሱ ዓመትም አጠናክራቸው ትቀጥሉ ዘንድ በተጨማሪ አደራ ልላችሁ እወዳለሁ፡፡
በመጨረሻም በአዲሱ ዓመት በ2015 ዓ.ም ካስመዘገብነው ውጤት በላቀ ደረጃ ስኬታማ የትምህርት ስራዎችን የምንሰራበት ፤ እጅ ለእጅ ተያይዘን የሀገራችንን ዘላቂ ሰላም የምናረጋግጥበት ፣ የምንረዳዳበት ፣ አቅመ ደካሞችን የምናግዝበት ፣ የሰላም የጤና እንዲሁም የብልፅግና ዘመን እንዲሆንልን ከልብ እመኛለሁ።
መልካም አዲስ ዓመት!
ክቡር ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ደሙ
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ
0 Comments