እንኳን ለ 2015 ዓ.ም አዲስ ዓመት በሰላም በፍቅር እና በጤና አደረሰን ፤ አደረሳችሁ!

ቀን 4/13/2014 ዓ.ም

እንኳን ለ 2015 ዓ.ም አዲስ ዓመት በሰላም በፍቅር እና በጤና አደረሰን ፤ አደረሳችሁ!

አዲስ ዓመት አዲስ ተስፋን እና ትጋትን የሚያላብስ የአዲስ ምስራፍ መጀመሪያ እንደመሆኑ መጠን በአደይ አበባዎች ታጅበን ፤ አረንጋዴ ጸዳል ተላብሰን ፤ አበባን አየሁሽ ብለን ፤ ከወዳጅ ከዘመድ ጋር እንኳን ከዘመን ዘመን አሽጋገራችሁ ተባብለን ፤ በደስታ የምንቀበለው እና ከአለም ብቸኛው በሆነው የዘመን አቆጣጠር ከአስራ ሶስት ወራት በሀላ የሚመጣ ልዩ የውበት መገለጫ ቀን ነው፤ አዲስ ዓመት፡፡

አዲስ ዓመት ከአዲስ ህልም እና ህልሙን ለማሳካት ከምናስቀምጠው እቅድ ጋር እጅጉኑ የተቆራኘ ነው፡፡ በመሆኑም በአዲስ ዓመት ልናካውናቸው ያስቀመጥናቸውን እቅዶቻችንን ለማሳካት የሚቻለን ካለፈው አፈጻጸማችን መነሳት ስንችል መሆኑን መዘንጋት ተገቢ አይድለም፡፡

እንደ ሀገር ባሮጌው ዓመት ከነበሩን አፈጻጸምች መካከል በእልውናውም ሆነ ሀገርን በማዳን ዘመቻው ከደጀን እስከ ግንባር የነበረን አበርክቶ በወርቅ መዝገብ ውስጥ የተፃፈ ታላቅ ታሪክ ነው፡፡

ይህንንም በማጎልበት ሀገራችን ዳግመኛ ለሶስተኛ ጊዜ የተከፈተባትን ጦርነት ለመመከት እና ዘላቂ ሰላም እንዲረጋገጥ ለማድረግ በአዲስ ዓመትም ከመከላከያ ጎን በመቆም የሚናችንን ልንወጣ ይገባል፡፡ ምክያቱም ልጅ ወልደን የምናሳድገው ፣ ስርተን የምንገባው ፣ ጎርሰን የምናድረው ብሎም እንዲህ ከዘመን ዘመን የምንሻገረው በሀገራችን ሰላም ሲረጋገጥ በመሆኑ ነው፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የ2014 የትምህርት ዘመን ያሰመዘገብናቸውን የላቁ የትምህርት ስራዎችን አፈጻጸሞን በተሻለ ትግበራ ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስም ሆነ እጥረቶቻችንን ለማረም የምንችለው ለሀገራችን ሰላም የሚናችን መወጣት ስንችል ነው፡፡

ከዚህም ጎን ለጎን በ2014 የትምህርት ዘመንም በትምህርት ዘርፍ ስራችን ፍራማ ተግባራት ለማከናወን ችለናል፡፡ ይህ እንዲሆን የተማሪዎች ፣ የመምህራን ፣ የትምህርት ባለድርሻ አካላት እና የትምህርት አመራሮች ሚና የጎላ በመሆኑ ምስጋና ላቀርብ እወዳለሁ፡፡ በተጨማሪም አዲሱ ስርዓተ ትምህርት ወደ ሙሉ ትግበራ እና ወደ ሙከራ ትግበራ በሚገባባቸው የትምህርት ተቋማት ላይ ተገቢውን ርብርብ በማድረግ ውጤታማ እንዲሆን እንደምተደርጉም ሙሉ እምነት አለኝ፡፡

ለሀገር እንዲሁም ለትምህርት ተቋማት ሰላም እና መረጋጋት የትምህርት ማህበረሰቡ አካላት ከዚህ ቀደም ስታደርጉት የነበረውን አስተዋጽዎ በአዲሱ ዓመትም አጠናክራቸው ትቀጥሉ ዘንድ በተጨማሪ አደራ ልላችሁ እወዳለሁ፡፡

በመጨረሻም በአዲሱ ዓመት በ2014 ዓ.ም ካስመዘገብነው ውጤት በላቀ ደረጃ ስኬታማ የትምህርት ስራዎችን የምንሰራበት ፤ ከሀገር መከላከያ ጎን በመቆም የበኩላችንን አስተዋጽዎ የምናደርግበት ፤ እጅ ለእጅ ተያይዘን የሀገራችንን ዘላቂ ሰላም የምናረጋግጥበት ፣ የምንረዳዳበት ፣ አቅመ ደካሞችን የምናግዝበት ፣ የሰላም የጤና እንዲሁም የብልፅግና ዘመን እንዲሆንልን ከልብ እመኛለሁ።

መልካም አዲስ ዓመት!

ፈጣሪ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቻን ይባርክ!

ክቡር ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ደሙ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ

ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ!

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!’

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

መረጃዎችን በፍጥነት ለማግኘት ማሰፈንጠሪያዎቹን ይጫኑ!

You Tube: https://www.youtube.com/watch?v=TWkBGoeYCNQ…

Telegram ፡ https://t.me/wwwAddisAbabaeducationbureau

Twitter ፡ https://twitter.com/aacaebc

Face book: https://www.facebook.com/aacityeducationcommunication

Blog: – http://www.aacaebc.wordpress.com/

Website: – aaceb.gov.et

Email;- aacaebc@gmail.com

Instagram: – https://www.instagram.com/aacaeb/

aeb/

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 70
  • 222
  • 1,624
  • 6,404
  • 214,665
  • 214,665