እንኳን ለኢሬቻ በዓል በሠላም አደረሳችሁ!

by | ዜና

ቀን 20 /1/2015 ዓ.ም

እንኳን ለኢሬቻ በዓል በሠላም አደረሳችሁ!

ኢሬቻ የሰላም፣ የፍቅር፣ የአንድነት እና የወንድማማችነት የምስጋና በዓል በመሆኑ በህዝቦች መካከል ወንድማማችነትን ለማጠናከር የጋራ የሆኑ እሴቶቻችንን ለማጎልበት ያግዛል፡፡

ኢሬቻ በህዝብ መሰባሰብ አብሮነትን በሚያሳይ ደረጃ ደምቆ የሚከበር ሲሆን የኦሮሞ ሕዝብ የክረምቱን የጨለማ ጊዜ አሳልፈኸን ብራን ልምላሜን ውበትን ያሳየኸን፤ ተፈጥሮን ሕይወትን መልሰህ ያጎናፀፍከን፤ መሬቱን በልምላሜ፣ ድፍርሱን በጥራት የተካህልን፤ ወደ ብርሃንና መልካም ዘመን ያሻገርከን ፈጣሪያችን ምስጋና ይገባሃል በማለት ምስጋናውን የሚያቀርብበት እና ላጠፋነው ነገር ሁሉ ይቅር በለን እያለ ከፈጣሪው ጋር ጥልቅ ተፈጥሯዊ እና ሥነ-ልቦናዊ ግንኙነቱን የሚያጠናክርበት ታላቅ በዓል ነው።

ኢሬቻ ማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ሀብት ከመሆኑም ባሻገር የአንድነትን ፣ የብሮነትን እና የመተባበርን ስሜት የሚፈጥር ታላቅ በዓል በመሆኑ በዓሉን ስናከብር ይህንን በሚያሳይ ደረጃ ሊሆን ይገባል፡፡

ከዚህም በተጨማሪ ኢሬቻ በዩኔስኮ የተመዘገበ ሀብት በመሆኑ ሁሉም በእኔነት ስሜት በሰላማዊ መንገድ እንዲከበር የጋራ እና ከፍተኛ በሆነ ርብርብ የድርሻውን እንዲወጣ ጥሪዩን እያቀረብኩ በዓሉ የሰላም የፍቅር እና የጤና እንዲሆንላችሁ እመኛለሁ፡፡

አመሰግናለሁ!

ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ደሙ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ

ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!’

የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!

ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ባልታጠበ እጅ አይንዎን አፍዎን እና አፍንጫዎን ባለመንካት በዙሪያዎ ላሉ ሰዎች አርአያ ይሁኑ!

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 0
  • 175
  • 2,114
  • 9,135
  • 234,185
  • 234,185