እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሰን !

by | ዜና

(መስከረም 16/2016 ዓ.ም) በ326 ዓ.ም. የቄሳር ቆስጠንጢኖስ እናት ንግሥት እሌኒ ኪራቆስ በተባለ አንድ የታሪክ አዋቂና ሽማግሌ ጠቋሚነት መስቀሉ የተጣለበትን አካባቢ ተረዳች።  ከዚያም በኋላ ደመራ ደምራ በእሳት ባቀጣጠለችው ጊዜ ጢሱ ወደ ላይ ከወጣ በኋላ ተመልሶ ያረፈበትን ሥፍራ አስቆፍራ መስቀሉን አውጥታዋለች። ንግሥተ እሌኒ በጭሱ ምልክትነት መስቀሉን ለማውጣት ለሰባት ወራት ያህል ማስቆፈሯ ይነገራል። ዛሬ በኦርቶዶክስ ምዕመናን ዘንድ ደመራ የሚደመረውም ይህንን ታሪክ ተከትሎ እንደሆነ የሊቃውንቱ ምስክርነት አለ።

ለዛም ነው መስቀል የአዲስ ምዕራፍ መጀመሪያ የስኬት ማሳያ እንደሆነ እና  ደመራ የሁለንተናዊ አንድነት መገለጫ መሆኑ የሚወሳው፡፡ ከዚህም በመነሳት የዘንድሮውን የመስቀል ደመራ በዓልን ስናከብር በፍቅር በመረዳዳትና ለሀገራችን ሰላም መረጋገጥ ሚናችንን በመወጣት ሊሆን ይገባል፡፡

የዘንድሮ የመስቀልና የደመራ በዓልን ስናከብር የ2016 የትምህርት ዘመን የትምህርት ልማት ስራችን ውጤታማ እንዲሆን በ2015 የትምህርት ዘመን የተከናወኑ ስራዎች መነሻነት እጅግ ወሳኝ በመሆኑና የተከናወኑ የትምህርት ልማት ስራዎች የላቀ በመሆናቸው  መስጋናዩን እያቀረብኩ ለቀጣዩ ስራዎችን በትጋት እንድንሰራ አዳራ ለማለት እወዳለሁ፡፡

በመጨረሻም ለኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ እና ለደመራ በዓል በሰላም አደረሳችሁ በዓሉ የሰላም ፣ የፍቅር እና የደስታ እንዲሆንላችሁ ምኞቴን እገልጻለሁ፡፡

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 205
  • 158
  • 7,078
  • 31,331
  • 147,475
  • 147,475