ኢሬቻ በህዝብ መሰባሰብ አብሮነትን በሚያሳይ ደረጃ ደምቆ የሚከበር ፤ የኦሮሞ ሕዝብ የክረምቱን የጨለማ ጊዜ አሳልፈኸን ብርሀን ልምላሜን ያሳየኸን ፤ የተፈጥሮን ሕይወት መልሰህ ያጎናፀፍከን ፤ መሬቱን በልምላሜ፣ ድፍርሱን በጥራት የተካህልን፤ ወደ ብርሃንና መልካም ዘመን ያሻገርከን ፈጣሪያችን ምስጋና ይገባሃል በማለት ምስጋናውን የሚያቀርብበት እና ላጠፋነው ነገር ሁሉ ይቅር በለን እያለ ከፈጣሪው ጋር ጥልቅ ተፈጥሯዊ እና ሥነ-ልቦናዊ ግንኙነቱን የሚያጠናክርበት በዓል ነው።

by | ዜና

የሰላም፣ የፍቅር፣ የአንድነት እና የወንድማማችነት የምስጋና በዓል የሆነው ኢሬቻ  በህዝቦች መካከል ወንድማማችነትን ለማጠናከር የጋራ የሆኑ እሴቶቻችንን ለማጎልበት ይረዳል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ  ማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ሀብት ከመሆኑም ባሻገር የአንድነትን ፣ የብሮነትን እና የመተባበርን ስሜት የሚፈጥር ነው፡፡

ስለሆነም ይህ ታላቅ በዓል በሰላማዊ መንገድ እንዲከበር የድርሻችንን እንድንወጣ ጥሪዩን እያቀረብኩ በዓሉ የሰላም የፍቅር እና የጤና እንዲሆን እመኛለሁ፡፡

እንኳን ለኢሬቻ በዓል በሠላም አደረሳችሁ!

 

አመሰግናለሁ!

ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ደሙ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 205
  • 158
  • 7,078
  • 31,331
  • 147,475
  • 147,475