አዲሱን ስርዓተ ትምህርት መሰረት አድርጎ የተዘጋጀውን የግብረገብ ትምህርት መማሪያ መጽሀፍ እና የመምህር መምሪያ ለሚያስተዋውቁ መምህራን የአሰልጣኞች ስልጠና ተሰጠ፡፡

by | ዜና

(አዲስ አበባ 2/13/2015 ዓ.ም) የአሰልጣኞች ስልጠናው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ከ1ኛ እስከ 6ኛ ክፍል በአማርኛ እና አፋን ኦሮሞ ስርአተ ትምህርት ለሚያስተምሩ መምህራን በትምህርቱ ይዘቱ  ዙሪያ በቂ ግንዛቤ  እንዲኖራቸው ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን ከስልጠናው አዘጋጆች ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በስርአተ ትምህርት ማበልጸግና ትግበራ ዳይሬክቶሬት የግብረገብና ዜግነት ስርአተ ትምህርት ዝግጅት ባለሙያ አቶ ገበየሁ አስፋው  መርሀግብሩን አስመልክቶ በሰጡት አስተያየት  አዲሱን ስርአተ ትምህርት መሰረት በማድረግ በትምህርት ሚኒስቴር የተዘጋጀውን የግብረ ገብ ትምህርት ወደ አማርኛ መተርጎሙን እና የከተማውን አውድ መሰረት አድርጎ መዘጋጀቱን  ጠቁመው  መምህራኑ በትምህርት አይነቱ  ይዘት ዙሪያ  በቂ ግንዛቤ ይዘው ወደ መማር ማስተማር ስራው መግባት እንዲችሉ በማሰብ መዘጋጀቱን አስታውቀዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በአፋን ኦሮሞ ስርአተ ትምህርት ማበልጸግና ትግበራ ዳይሬክቶሬት የግብረገብና ዜግነት  ትምህርት ዝግጅት ባለሙያ አቶ መለሰ ዘለቀ በበኩላቸው በትምህርት ሚኒስቴር የተዘጋጀው የግብረገብ (barnoota safuu) ትምህርት ወደ አፋን ኦሮሞ መተርጎሙን ገልጸው  ስልጠናው በትምህርት አይነቱ የሚያስተምሩ መምህራን በይዘቱ ላይ በቂ ግንዛቤ እንዲያገኙ ከማስቻሉ ባሻገር በየትምህርት ቤቱ ለሚገኙ ቀሪ መምህራን በተመሳሳይ የመጽሀፉን ይዘት እንዲያስተዋውቁ የሚያግዛቸው መሆኑንም ጠቁመዋል፡፡

የአሰልጣኞች ስልጠናውን ቀደም ሲል ከትምህርት ሚኒስተር የተዘጋጀውን የግብረገብ ትምህርት መጽሀፍ ወደ አማርኛ እና አፋን ኦሮሞ ቋንቋዎች የተረጎሙና በትምህርት አይነቱ በቂ ልምድ ያላቸው መምህራን የሰጡ ሲሆን የትምህርት አይነቱ  ከ2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ ቀደም ብሎ መገለጹ ይታወቃል፡፡

 

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 308
  • 374
  • 4,289
  • 15,619
  • 98,485
  • 98,485