የትርጉም ስራው ከ1ኛ እስከ 6ኛ ክፍል ላለው የትምህርት እርከን የተዘጋጀውን የተማሪዎች መማሪያ መጽሀፍ፤የመምህር መምሪያ እንዲሁም መርሀ ትምህርቱን የሚያካትት መሆኑን በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የስርዓተ ትምህርት ማበልጸጊያና ትግበራ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ታለማ ገልጸው በትርጉም ስራው ከ2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በተመረጡና ሁለተኛ ዲግሪ ባላቸው የእንግሊዘኛ እና ሲቪክስ መምህራን ተሳታፊ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡
ዳይሬክተሩ አክለውም የግብረገብ ትምህርት መጽሀፍ የመተርጎምም ሆነ ከአዲስ አበባ ተጨባጭ ሁኔታ ጋር የማስማማት ስራው ሲጠናቀቅ በየደረጃው ከመምህራን እና ሌሎች ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በሚደረግ ውይይት ብቃቱ ተረጋግጦ ወደህትመት እንደሚገባ በመግለጽ በአዲስ አበባ በ2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ከ1ኛ እስከ 6ኛ ክፍል ለሚማሩ ተማሪዎች የግብረገብ ትምህርት እንደሚሰጥም አስረድተዋል፡፡
0 Comments