አዲሱን ስርአተ ትምህርት መሰረት አድርጎ የተዘጋጀውን የክወና እና የእይታ ጥበባት (performing and visual art)ትምህርት ለሚያስተምሩ መምህራን የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ።

by | ዜና

(ቀን ህዳር 16/2016 ዓ.ም) በግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው ከሁሉም ክፍለ ከተሞች የተመለመሉና ከሙዚቃ ትምህርት ጋር በተገናኘ በቂ ግንዛቤ የሌላቸው መምህራን የተሳተፉ  ሲሆን መምህራኑ በዚህ ስልጠና ያገኙትን ግንዛቤ መሰረት አድርገው በየትምህርትቤታቸው ለሌሎች መምህራን በተመሳሳይ ሁኔታ ግንዛቤ የማስጨበጥ ተግባር የሚያከናውኑ ይሆናል።

ስልጠናው በዋናነት መምህራኑ ለትምህርት አይነቱ የተዘጋጀውን የመጽሀፍ ይዘት በአግባቡ ተረድተው ማስተማር እንዲችሉ መሰረታዊ ግንዛቤ እንዲኖራቸው ታስቦ መዘጋጀቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የስነ ጥበባት ትምህርት ዝግጅት ባለሙያ ወይዘሮ እየሩሳሌም በዳኔ አስታውቀዋል።

ባለሙያዋ አክለውም ከሙዚቃ ትምህርት ጋር በተገናኘ መምህራኑ ሙዚቃ እንዴት እንደሚጻፍም ሆነ እንደሚነበብና መሰረታዊ የሙዚቃ ድምጾች የትኞቹ እንደሆኑ በስልጠናው ግንዛቤ እንዲያገኙ መደረጉን ጠቁመው የሙዚቃ መሳሪያ ባላቸው ትምህርት ቤት የሚያስተምሩ መምህራን ተማሪዎቻቸውን መሰረታዊ የሙዚቃ ድምጾችን ማሳወቅ እንዲችሉ በተግባር የተደገፈ ስልጠና እንዲወስዱ መደረጉን አስገንዝበዋል።

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 30
  • 222
  • 1,584
  • 6,364
  • 214,625
  • 214,625