አዲሱን ስርአተ ትምህርት መሰረት አድርጎ የተዘጋጀውን የቅድመ አንደኛ እና አንደኛ ደረጃ ትምህርት ለቢሮው ሱፐርቫይዘሮች የማስተዋወቅ ስራ ተሰራ፡፡

by | ዜና

(አዲስ አበባ 23/1/2016 ዓ.ም)   በትውውቁ በአማርኛና አፋን ኦሮሞ ስርአተ ትምህርት ድጋፍ የሚያደርጉ ሱፐርቫይዘሮች የተሳተፉ ሲሆን የቢሮው ሱፐርቨይዘር የሆኑት አቶ ሰለሞን ወንድሙ እና አቶ ገመቺስ ፍቃዱ የስርአተ ትምህርቱን ይዘት በተመለከተ ገለጻ አድርገዋል፡፡

ስርአተ ትምህርቱን ማስተዋወቅ ያስፈለገው የቢሮው ሱፐርቫይዘሮች አዲሱን ስርአተ ትምህርት መሰረት አድርጎ በሁለቱም ስርአተ ትምህርት ከሚሰጠው ትምህርት አተገባበር ጋር በተገናኘ በቂ ግንዛቤ ይዘው በየትምህርትቤቱም ሆነ በክላስተር ማዕከላት ተገቢውን የድጋፍና ክትትል ስራ መስራት እንዲችሉ ለማድረግ መሆኑን  የቢሮው አጠቃላይ ትምህርት ሱፐርቪዥን ቡድን መሪ ትግስት ድንቁ እና የአፋን ኦሮሞ አጠቃላይ ሱፐርቪዥን ቡድን መሪ አቶ መንግስቱ አበበ አስታውቀዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ሱፐርቪዥን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ፀጋዬ አሰፋ በመርሀ ግብሩ ማጠቃለያ ባስተላለፉት መልዕክት የቢሮው ሱፐርቫይዘሮች ለቅድመ አንደኛም ሆነ አንደኛ ደረጃ የተዘጋጀውን ስርአተ ትምህርት መሰረት በማድረግ በየትምህርትቤቱ ተገቢውን የድጋፍና ክትትል ስራ በመስራት የተማሪዎችን ውጤትና ስነምግባር ለማሻሻል በሚሰራው ስራ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ማበርከት እንደሚጠበቅባቸው አስገንዝበዋል፡፡

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 205
  • 158
  • 7,078
  • 31,331
  • 147,475
  • 147,475