አዲሱን ስርአተ ትምህርት መሰረት አድርጎ የተዘጋጀውን የቅድመ አንደኛ ደረጃ መለማመጃ ደብተር እና የመምህር መምሪያ ለሚያስተዋውቁ መምህራን የአሰልጣኞች ስልጠና ተሰጠ፡፡

by | ዜና

(አዲስ አበባ 2/13/2015 ዓ.ም)  መርሀ ግብሩ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በሚገኙ የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በአማርኛ እና አፋን ኦሮሞ ስርአተ ትምህርት ለሚያስተምሩ መምህራን በትምህርቱ ይዘቱ  በቂ ግንዛቤ  እንዲኖራቸው ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን ከስልጠናው አዘጋጆች የተገኘው መረጃ ያሳያል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በስርአተ ትምህርት ማበልጸግና ትግበራ ዳይሬክቶሬት የቅድመ አንደኛ ደረጃ ስርአተ ትምህርት ዝግጅት ባለሙያ አቶ ነጋ ገረመው  እንዳስታወቁት አዲሱን ስርአተ ትምህርት መሰረት በማድረግ የስርአተ ትምህርት ክለሳ ከተካሄደባቸው የትምህርት እርከኖች መካከከል አንዱ የቅድመ አንደኛ ደረጃ  ትምህርት እንደመሆኑ መምህራኑ ከጀማሪ ጀምሮ በደረጃ አንድና ሁለት የተዘጋጁ የመለማመጃ ደብተሮች ይዘትና በመምህር መምሪያ ዙሪያ  በቂ ግንዛቤ ይዘው ወደ መማር ማስተማር ስራው መግባት እንዲችሉ በማሰብ ስልጠናው መዘጋጀቱን አስታውቀዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በአፋን ኦሮሞ ስርአተ ትምህርት ማበልጸግና ትግበራ ዳይሬክቶሬት የቅድመ አንደኛ ደረጃ ስርአተ ትምህርት ዝግጅት ባለሙያ አቶ አለማየሁ ጣሰው በበኩላቸው  ስልጠናው የመለማመጃ ደብተሩን እና የመምህር መምሪያውን ከማስተዋወቅ ባሻገር መምህራኑ ተማሪዎችን ወጥ በሆነ መልኩ መመዘን እንዲችሉ በከተማ ደረጃ  በተዘጋጀ ፎርም ዙሪያ በቂ ግንዛቤ እንደሚፈጥርላቸው ገልጸው ሰልጣኞቹ በቀጣይ በየትምህርት ቤቱ ለሚገኙ ቀሪ መምህራን  የትምህርት ይዘቱን በተመሳሳይ መልኩ እንደሚያስተዋውቁም ጠቁመዋል፡፡

አዲሱን ስርአተ ትምህርት መሰረት አድርጎ የተዘጋጀው የቅድመ አንደኛ ደረጃ ትምህርት በአዲስ አበባ ከተማ በ2015ዓ.ም በተመረጡ ትምህርት ቤቶች በሙከራ ደረጃ ተግባራዊ የተደረገ ሲሆን ስርአተ ትምህርቱ በ2016ዓ.ም በሁሉም ትምህርት ቤቶች ወደ ሙሉ ትግበራ እንደሚገባ ቀደም ብሎ መገለጹ ይታወቃል፡፡

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 308
  • 374
  • 4,289
  • 15,619
  • 98,485
  • 98,485