አራዳ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 በሚገኘው 5ኪሎ አጸደ ህጻናት ትምህርት ቤት ጉብኝት ተካሄደ፡፡

by | ዜና

(አዲስ አበባ ህዳር 28 ቀን 2016 ዓ.ም) በግብኝቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ  ፤ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዘዳንት ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ እንዲሁም የትምህርት ቢሮ ማኔጅመንት አባላትና የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

5ኪሎ አጸደ ህጻናት ትምህርት ቤትን የወረዳ 6 ሸማቾች ኃላፊነቱ የተወሰነ ህብረት ስራ ማህበር እያስተዳደረው የሚገኝ ሲሆን ትምህርት ቤቱ በዘንድሮ 190 ተማሪዎችን ተቀብሎ በ10 መምህራን በማስተማር ላይ እንደሚገኝ ከትምህርትቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

አጸደ ህጻናት ትምህርት ቤቱ 5 ኪሎ ከሚገኘው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲቲዩት አጠገብ እንደመገኘቱ በቀጣይ ትምህርትቤቱ ስታንዳርዱን የጠበቀ እንዲሆን እና ለተማሪዎቹ ምቹ የመማሪያ ስፍራ መሆን እንዲችል ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጋር በቅንጅት ለመስራት ታስቦ ጉብኝቱ መካሄዱን  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ አስታውቀዋል፡፡

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 27
  • 222
  • 1,581
  • 6,361
  • 214,622
  • 214,622