(ጥቅምት 28/2016 ዓ.ም) ድጋፉን የሚያደርጉት ቀደም ሲል በትምህርት ቤቱ የተማሩት የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ጀማል አህመድና በወቅቱ አብረዋቸው የተማሩ ጓደኞቻቸው ሲሆኑ በዛሬው እለት በአቶ ጀማል የተመራ የቀድሞ የትምህርት ቤቱ ተማሪዎች ቡድን ከአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ እና ከቢሮው ማኔጅመንት አባላት ጋር በመሆን በትምህርት ቤቱ ጉብኝት አካሂዱዋል፡፡
ቤተልሔም 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ከ1962 ዓ.ም ጀምሮ በማስተማር ላይ እንደሚገኝ እና በ2016 ዓ.ም 1,132 ተማሪዎችን ተቀብሎ በማስተማር ላይ እንደሚገኝ የትምህርት ቤቱ ርዕሰ መምህር አቶ ፍቃዱ ባለው ገልጸው ትምህርት ቤቱ በመማሪያ ክፍል እጥረት እና በላብራቶሪ ክፍሎች ማነስ ምክንያት ስታንዳርዱን የጠበቀ ትምህርት ለመስጠት መቸገሩን አስታውቀዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በበኩላቸው የትምህርት ለትውልድ ንቅናቄን መሰረት በማድረግ የትምህርት ቤቶችን ደረጃ ለማሻሻል በነበረው ዘመቻ በግንባር ቀደምትነት ፍቃደኛ ከሆኑ አካላት መካከል አንዱ የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ጀማል መሆናቸውን ጠቁመው ቤተልሔም 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ደረጃውን የጠበቀ የትምህርት አገልግሎት መስጠት እንዲችል እንዲሁም እነ አቶ ጀማል እና ሌሎች በትምህርት ቤቱ ተምረው ከፍተኛ ደረጃ የደረሱ የቀድሞ ተማሪዎችን አርአያ የሚከተሉ ተማሪዎችን እንዲያፈራ ድጋፉ የሚያበረክተው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡
ከህጻንነት ጀምሮ እስከ 8ኛ ክፍል ድረስ በትምህርት ቤቱ የነበራቸው ቆይታ አሁን ለደረሱበት ቦታ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ማበርከቱን የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ጀማል አህመድ ጠቅሰው ከሳቸው ጋር አንድ ባች የነበሩና በተለያዩ የአለም ሀገራት የሚገኙ 40 የሚሆኑ የቀድሞ የትምህርት ቤቱ ተማሪዎች ለትምህርት ቤቱ ድጋፍ ከማድረግ ባሻገር የቀድሞ መምህራኖቻቸውን ለመርዳት እንቅስቃሴ ላይ መሆናቸውንም አስረድተዋል፡፡
አቶ ጀማል አክለውም ትምህርት ቤቱ ቀደም ሲል በነበረው ቁመና ላይ እንዲገኝ የትምህርት ጥራትን መሰረት ያደረገ ስራ በመስራት የተማሪዎችን ውጤት ማሻሻል እንደሚገባ ገልጸው ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕም ከዚህ ጋር የተገናኘ ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
0 Comments