(ታህሳስ 21/2017ዓ.ም) የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ2017 ዓ.ም ስድስት ወራት በስትራቴጂክ እቅድ እና በአጠቃላይ የሪፎርም ስራዎች ያከናወናቸው ተግባራት ግምገማ ተካሂዷል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የቢሮ ኃላፊ አማካሪና የዘርፉ ሀላፊ ወይዘሮ አበበች ነጋሽ ቢሮው በ2017 ዓ.ም ስድስት ወራት በስትራቴጂክ እቅዱ ያስቀመጣቸው ግቦች አፈጻጸም እና በሪፎርም ስራዎች ያከናወናቸው ተግባራት ቀደም ሲል በየዘርፎቹ መገምገማቸውን ገልጸው ቢሮው በእቅድ ካስቀመጣቸው ተግባራት አንጻር አፈጻጸሙ በከፍተኛ ደረጃ ላይ እንደሚገኝ በሪፖርቱ መረጋገጡን አመላክተዋል።
በግምገማው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የእቅድና በጀት ዝግጅት ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጌታሁን ለማ ከቢሮ ጀምሮ በየደረጃው በስድስት ወር ስትራቴጂክ እቅዱን መሰረት በማድረግ የተከናወኑ ተግባራትን ሪፖርት አቅርበዋል።
የሪፎርም አገልግሎት አሰጣጥ ክትትልና ምዘና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ተስፋገኘሁ ለገሰ በበኩላቸው በ2017 ዓ.ም ስድስት ወራት ከመልካም አስተዳደርና አገልግሎት አሰጣጥ እንዲሁም ከቅንጅታዊ አሰራር እና አጠቃላይ የሪፎርም ስራዎች ጋር በተገናኘ የተከናወኑ ተግባራትን ሪፖርት በዝርዝር አቅርበው ውይይት ተካሂዷል።
0 Comments