(ህዳር 4/2017 ዓ.ም) ክትትልና ድጋፉ በሁሉም የመንግስት ትምህርት ቤቶች እና ወረዳ ትምህርት ጽህፈት ቤቶች በመካሄድ ላይ የሚገኝ ሲሆን በትላንትናው እለት ድጋፍና ክትትሉን ለሚያደርጉ ባለሙያዎች ኦረንቴሽን መሰጠቱን ከቢሮው የሪፎርምና አገልግሎት አሰጣጥ ክትትል ድጋፍና ምዘና ዳይሬክቶሬት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሪፎርምና አገልግሎት አሰጣጥ ክትትል ድጋፍና ምዘና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ተስፋገኘሁ ለገሰ ቀደም ሲል ተመሳሳይ የድጋፍና ክትትል ተግባር በክፍለ ከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤቶችና ቢሮ በሚገኙ ስራ ክፍሎች መካሄዱን ገልጸው ድጋፍና ክትትሉ በዋናነት ከሪፎርምና የአገልግሎት አሰጣጥ ሂደቱ ጋር በተገናኘ የተከናወኑ ተግባራትን ጨምሮ ከባለድርሻ አካላት ጋር ያለው ቅንጅታዊ አሰራር አፈጻጸም እንዲሁም የመሪ እቅድ ዝግጅትና አፈጻጸምን መሰረት አድርጎ በመካሄድ ላይ እንደሚገኝ አመላክተዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሪፎርምና አገልግሎት አሰጣጥ ክትትል ድጋፍና ምዘና ቡድን መሪ አቶ ሀፍቱ ብርሀኔ በበኩላቸው በትምህርት ተቋማት የሚካሄድ ክትትልና ድጋፍ ተቋማቱን ወደ ተቀራረበ የአፈጻጸም ደረጃ በማምጣት የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ በሚደረገው እንቅስቃሴ የበኩላቸውን አስተዋጽኦ ማበርከት እንዲችሉ የሚኖረው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን ጠቁመው የክትትልና ድጋፉ ግብረመልስ ለሁሉም ተቋማት የሚቀርብ መሆኑን አስገንዝበዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የሪፎርምና አገልግሎት አሰጣጥ ክትትል ድጋፍና ምዘና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ተስፋገኘሁ ለገሰ ከቡድን መሪው አቶ ሀፍቱ ብርሀኔ ጋር በመሆን ክትትልና ድጋፉ እየተካሄደባቸው ከሚገኙ ተቋማት መካከል በተወሰኑ ወረዳ ጽህፈት ቤቶችና ትምህርት ቤቶች ተገኝተው ምልከታ አድርገዋል።
ቢሮው በትምህርት ተቋማት የዝግጅት ምዕራፍ አፈጻጸምን መሰረት ያደረገ ክትትልና ድጋፍ ማካሄድ ጀመረ።
0 Comments