ቢሮው በበጀት አመቱ 9 ወራት ከተለያዩ ሴክተር መስሪያ ቤቶች ጋር በቅንጅት ባከናወናቸው ተግባራት ዙሪያ ውይይት ተካሄደ።

by | ዜና

(ቀን ሚያዚያ 24/ 2016 ዓ.ም) ውይይቱ የመልካም አስተዳደር ችግሮችን በቅንጅታዊ አሰራር በመፍታትና የሪፎርም ስራዎችን ለማጠናከር በ9ወር የተከናወኑ ተግባራትን መሰረት አድርጎ የተካሄደ ሲሆን የቢሮው የሪፎርም አገልግሎት አሰጣጥ ክትትል ድጋፍና ምዘና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዳዊት ከበደ በ9 ወር ውስጥ ከ24 ሴክተር መስሪያ ቤቶችና  አደረጃጀቶች ጋር በቅንጅት የተ ከናወኑ ተግባራትን ሪፖርት አቅርበው ውይይት ተካሂዷል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ በውይይቱ መክፈቻ ባስተላለፉት መልዕክት ቢሮው በስነ ምግባሩ ምስጉን ሆኖ በዕውቀትና ክህሎት የዳበረ ትውልድ ለመፍጠር የሚያከናውናቸው ተግባራት ውጤታማ መሆን የሚችሉት ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት መስራት ሲችል መሆኑን ጠቁመው በበጀት አመቱም በቅንጅት የተለያዩ ተግባራት መከናወናቸውን በመግልጽ በቀጣይ በተለይም ሀምሌ ወር ኦን ላይን የሚሰጠው የ2016ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በታቀደው መርሀግብር መሰረት እንዲሰጥ ሁሉም ባለድርሻ አካል የግብአት ድጋፍ ከማድረግ ጀምሮ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የቢሮ ኃላፊ አማካሪና የዘርፉ ሀላፊ ወይዘሮ አበበች ነጋሽ በበኩላቸው ውይይቱ ቢሮው ከተለያዩ ሴክተር መስሪያ ቤቶችም ሆነ  አደረጃጀቶች ጋር በቅንጅት ባከናወናቸው ተግባራት የተገኙ ውጤቶችና በአፈጻጸም የተስተዋሉ ጉድለቶች ላይ በመወያየት በቀጣይ የተሻለ ስራ መስራት እንዲቻል ታስቦ መዘጋጀቱን ገልጸዋል።

የአዲስ አበባ ምክር ቤት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ወይዘሮ ዘይነባ ሽኩር በውይይቱ ማጠቃለያ  እንዳስታወቁት የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ከተለያዩ ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት በመ ስራትና የተከናወኑ ተግባራትን በመገምገም በከተማ ደረጃ ግንባር ቀደም ከሆኑ ተቋማት መካከል አንዱ መሆኑን ገልጸው  የትምህርት ስራ የሁሉንም ባለድርሻ ተሳትፎ የሚፈልግ እንደመሆኑ በቀጣይ ቅንጅታዊ ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።

የውይይቱ ተ ሳታፊ የሴክተር መስሪያ ቤት አመራሮችና ተወካዮች ትምህርት ቅንጅታዊ አሰራርን ከሚፈልጉ ሴክተሮች መካከል አንዱ በመሆኑ በአመቱ መጀመሪያ ከቢሮው ጋር በመፈራረም ወደተግባር መግባታቸውን ጠቁመው በ9 ወራቱ በቅንጅት በተሰሩ ስራዎች አበረታች ውጤት መመዝገቡንም አስታውቀዋል።

0 Comments

SITE VISITORS

  • 0
  • 187
  • 249
  • 2,423
  • 8,975
  • 243,957
  • 243,957