ምልከታው በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የልዩፍላጎት/አካቶ ትምህርትና የጎልማሶች መሰረታዊ ትምህርት ዳይሬክቶሬት አስተባባሪነት የክፍለከተማ የዘርፉ ቡድን መሪዎችና ባለሙያዎችን ጨምሮ በቢሮ ሱፐርቫይዘሮችና ባለሙያዎች የተካሄደ ሲሆን በዛሬው እለት በድጋፍ መስጫ ማዕከላቱ የታዩ ጠንካራና ደካማ ጎኖችን መሰረት በማድረግ ውይይት ተካሂዱዋል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የልዩፍላጎት/አካቶ ትምህርትና የጎልማሶች መሰረታዊ ትምህርት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዳንኤል አስራት ምልከታው በዋናነት የተሻለ አፈጻጸም ያላቸውን የድጋፍ መስጫ ማዕከላት በመለየት የልምድ ልውውጥ ለማድረግና አፈጻጸማቸው ዝቅተኛ በሆኑ ማዕከላት ደግሞ አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ታስቦ መካሄዱንም ገልጸዋል፡፡
ዳይሬክተሩ አክለውም የድጋፍ መስጫ ማዕከላቱ ለልዩ ፍላጎት ተማሪዎች ድጋፍ የሚሰጡ እንደመሆናቸው በቀጣይ አሁን ካሉት 78 ማዕከላት በተጨማሪ ሌሎች አዳዲስ የድጋፍ መስጫ ማዕከላት እንደሚከፈቱም አስረድተዋል፡፡
0 Comments