በ6 ወራት በአገልግሎት አሰጣጥ ምዘና ከ1-3 ለወጡ የቢሮ ዳይሬክቶሬቶች እውቅናና ሽልማት ተሰጠ፡፡

by | ዜና

(ቀን ጥር 25/2016 ዓ.ም)  የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ በ2016 የትምህርት ዘመን የመጀመሪያ ስድስት ወራት በአገልግሎት አሰጣጥና በሪፎርም ስራዎች አፈጻጸም ምዘና ከ1 እስከ 3 ለወጡ የቢሮ ዳይሬክቶሬቶች እውቅናና ሽልማት ሰጥቷል፡፡

 

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ  የሪፎርም አገልግሎት አሰጣጥ ክትትል ድጋፍና ምዘና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ዳዊት ከበደ  ባቀረቡት ሪፖርት ላይ ዳይሬክቶሬቱ የ2016 የትምህርት ዘመን የመጀመሪያ ግማሽ ዓመት የ6 ወራት የሪፎርምና አገልግሎት አሰጣጥ ውጤታማነትን አስመልክቶ የመመዘኛ መስፈርት በማዘጋጀት ሁሉንም የቢሮ ዳይሬክቶሬቶች ምዘና ማካሄዱን በመግለጽ ምዘናው ከመከናወኑ በፊት 3 ጊዜ ድጋፍና ክትትል እንዲሁም 2 ጊዜ ፍረጃ መከናወኑን አመላክተዋል፡፡

በምዘናዉም ከአላማ ፈጻሚ ዳይሬክቶሬቶች  መካከል 1ኛ የአማርኛ ዘርፍ የስርዓተ ትምህርት ማበልፀጊያ እና ትግበራ ደይሬክቶሬት ፣ 2ኛ የአጠቃላይ ትምህርት ሱፐር ቪዥን ዳይሬክቶሬትና 3ኛ የትምህርት ቴክኖሎጂና መረጃ ዳይሬክቶሬት ፤ ከደጋፊ ዳይሬክቶሬቶች መካከል  1ኛ የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ፣ 2ኛ  የእቅድና በጀት ዝግጅትና ክትትል ዳይሬክቶሬትና 3ኛ የፋይናንስ ዳይሬክቶሬት በመውጣት እውቅናና ሽልማት የተሰጣቸዉ ሲሆን ለምዘናው መሳካት አስተዋጽዎ ላበረከተዉ ለሪፎርም አገልግሎት አሰጣጥ ክትትል ድጋፍና ምዘና ዳይሬክቶሬትም ከመድረክ እውቅና ተሰጥቷል፡፡

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

https://twitter.com/aacaebc

SITE VISITORS

  • 0
  • 184
  • 249
  • 2,420
  • 8,972
  • 243,954
  • 243,954