(ጥቅምት 5/2017 ዓ.ም) የድጋፍ መስጫ ማዕከላቱ በ11 አንደኛ ደረጃ ትምህርትቤቶች የተቋቋሙ ሲሆን ለማዕከ ላቱ ግምታቸው ከ570,000 ብር የሚሆን የግብአት ድጋፍ መደረጉን ከቢሮው የልዩ ፍላጎትና አካቶ ትምህርት የስራ ክፍል የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
ለድጋፍ መስጫ ማዕከላቱ የሜንቶሶሪ እቃዎች ማለትም ዊለቸሮችና ክራንቾችን ጨምሮ የተለያዩ የአካል ድጋፍ ቁሳቁሶች መሰራጨታቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የልዩ ፍላጎት አካቶ ትምህርት ባለሙያ አቶ ጸጋዬ ሁንዴ ጠቁመው በተመሳሳይ ለማእከላቱ ለልዩ ፍላጎት ተማሪዎች አገልግሎት የሚውሉ የትምህርት መርጃ መሳሪያዎች ድጋፍ መደረጉን አመላክተዋል፡፡
0 Comments