በ2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በተማሪ ምዝገባ የመረጃ አሰባበሰብ ዙሪያ ውይይት ተካሄደ፡፡

by | ዜና

(አዲስ አበባ 11/1/2016 ዓ.ም) ውይይቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ትምህርት መረጃ ስርአት ስራ አመራር ቡድን ያዘጋጀው ሲሆን በመርሀ ግብሩ የክፍለከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት የዘርፉ ባለሙያዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

ለ2016ዓ.ም የትምህርት አመት በየትምህርትቤቱ እየተካሄደ የሚገኘው የተማሪ ምዝገባ መረጃ አሰባሰብ ቀደም ሲል ከነበረው አንጻር አፈጻጸሙ የተሻለ መሆኑነ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ትምህርት መረጃ ስርአት ስራ አመራር ቡድን መሪ አቶ ደስታ አብረሀም በውይይቱ ገልጸው የምዝገባ ወቅቱ እስኪጠናቀቅ የተማሪ ቅበላ መረጃውን በአግባቡ በማደረጃት አንድም ህጻን ከትምህርት ገበታ ውጪ እንዳይሆን መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡


የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የትምህርት ቴክኖሎጂና መረጃ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ደረጀ ዳኜ በበኩላቸው በትምህርት ሴክተሩ ለሚከናወኑ የተለያዩ ተግባራት ውጤታማነት የተማሪ ቁጥር ወሳኝ እንደመሆኑ ጥራቱን የጠበቀ መረጃ ማደራጀት እንደሚገባ ገልጸው ለ2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን በመካሄድ ላይ ከሚገኘው የተማሪ ምዝገባ መረጃ አሰባበሰብ ጋር በተገናኘ እስካሁን ያለውን ጠንካራ ጎን በማስቀጠልና በሂደት የተስተዋሉ ክፍተቶችን በማረም ደረጃውን የጠበቀ መረጃ በማደራጀት ወደ ሚመለከተው አካል መላክ እንደሚገባ አስታውቀዋል፡፡

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 205
  • 158
  • 7,078
  • 31,331
  • 147,475
  • 147,475