በ2015 የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከፍተኛው ውጤት ከአዲስ አበባ ከተማ 649 ሆኖ ተመዘገበ::

by | ዜና

(አዲስ አበባ 28/1/2016 ዓ.ም) በ2015 የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ከአዲስ አበባ ከተማ 649 ከፍተኛ ውጤት መሆኑን እና በተፈጥሮ ሳይንስ የትምህርት ዘርፍ የተመዘገ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በ 2015 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ውጤትና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን አስመልክቶ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ በማህበራዊ ሳይንስ 533 ከደብረ ማርቆስ ከተማ ከፍተኛ ውጤት ሆኖ መመዝገቡን ተናግረዋል፡፡

በፈተናው ከ50 በመቶ በላይ ያገኙ ተማሪዎች 27 ሺህ 267 ተማሪዎች መሆናቸውን የገለፁት ሚኒስትሩ፤ ይህም በመቶኛ ሲሰላ 3 ነጥብ 2 ብቻ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 184
  • 249
  • 2,420
  • 8,972
  • 243,954
  • 243,954