(ጥቅምት 29/2017 ዓ.ም) በአሰልጣኞች ስልጠና መርሀ ግብሩ የክፍለከተማ ትምህርት ጽህፈት ቤት የሁለቱ ስርአተ ትምህርት ትግበራ ቡድን መሪዎችን ጨምሮ የሶሻል ሳይንስ ትግበራ ባለሙያዎች እና የስራ አስተባባሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
የዘንድሮው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን ለ19ኛ ጊዜ ሀገራዊ መግባባት ለሕብረ ብሔራዊ አንድነት በሚል መሪቃል እንደሚከበር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የስነምግባር መሻሻልና የተማሪ ጉዳይ ባለሙያ አቶ ባይሳ ፀጋዬ ገልጸው በትምህርት ሴክተሩ ቀኑ በድምቀት እንዲከበር ከወዲሁ የቅድመ ዝግጅት ስራዎችን በአግባቡ መስራት እንዲቻል ታስቦ የአሰልጣኞች ስልጠናው መዘጋጀቱን አስታውቀዋል፡፡
ባለሙያው አያይዘውም የትምህርት ማህበረሰቡ 19ኛውን የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን ሲያከብር ተማሪዎች ከፌደራሊዝም እና ከህገ መንግስቱ ጋር በተገናኘ በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸው የተለያዩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን በአግባቡ መስራት እንደሚገባ ጠቁመው ቢሮው ቀኑ በትምህርት ቤቶች በድምቀት እንዲከበር ተገቢውን የድጋፍና ክትትል ስራ የሚሰራ መሆኑንም አመላክተዋል፡፡
በ19ኛው የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን አከባበር ጋር በተገናኘ የአሰልጣኞች ስልጠና ተሰጠ፡፡
0 Comments