በግዢና ፋይናንስ መመሪያዎች ላይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ ::

by | ዜና

(አዲስ አበባ ህዳር 24/2016 ዓ.ም )የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ፋይናንስ አስተዳደር ግዥና የለውጥና መልካም አስተዳደር ዳይሬክቶሬቶች በፋይናንስ አስተዳደርና ግዢ መመሪያ  እንዲሁም የጨረታ አከፋፈት ላይ ለዘርፉ ባለሙያዎችና ለሚመለከታቸው አካላት ስልጠና ሰጡ ::

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የፋይናንስ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ መክብብ በግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠናው ላይ እንዳሉት ስልጠናው አዲስ ስራውን የተቀላቀሉ ባለሙያዎች በአሰራሩ ላይ በቂ ግንዛቤ እንዲኖራቸውና በስራው ላይ የቆዩ ባለሙያዎችም ከልምድ ባለፈ ስራውን በእውቀት በመስራት ያለውን ተጠያቂነትና የስጋት አቅጣጫዎች እንዲለዩ ያግዛል ሲሉ ተናግረዋል ::

ስልጠናው የፋይናንስ ቢሮ ግዥ ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ዮሐንስ የተሰጠ ሲሆን በአጠቃላይ ፋይናንስ አስተዳደር ደንቦችና የክፍያ ስርዓት ፣ በመንግስት ግዢ አካሄድ እንዲሁም የንብረት አያያዝ ላይ ዋና ትኩረት አድርጓል ::

ስልጠናው በሁለተኛ ቀን ውሎው በጨረታ ሰነድ አዘገጃጀትና አከፋፈት መስፈርቶችና ልዩ ባህሪ እንዲሁም የአገልግሎት ግዥና ልዩ ባህሪያቶች ላይ የፋይናንስ ቢሮ ሙያዊ ድጋፍና ስልጠና ከፍተኛ ባለሙያ በሆኑት አቶ ደሳለኝ ተሰጥቶ በተሳታፊዎች ውይይት ተደርጎበታል ::

 

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 27
  • 222
  • 1,581
  • 6,361
  • 214,622
  • 214,622