በደጅ አዝማች ባልቻ አባ ነፍሶ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት የመስክ ምልከታ ተካሄደ።

by | ዜና

(ቀን ጥር 20/2016 ዓ.ም)  በአዲስ አበባ ከተማ ም/ቤት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ዘርፍ ቋሚ ኮሚቴ አባላት በደጅ አዝማች ባልቻ አባ ነፍሶ ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤት በመገኘት በትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ  የተከናወኑ ስራዎችን አመልክቶ ምልከታ አካሂደዋል።

በምልከታው የመማሪያ ክፍሎች ፣ ቤተ ሙከራዎች ፣ ቤተ መጻሕፍት ፣ የመምህራን  ማረፊያን እንዲሁም መማር ማስተማሩን ስኬታማ ለማድረግ የተከናወኑ ተግባራት ተዳሰዋል።

በአዲስ አበባ ከተማ ም/ቤት የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት እንደተናገሩት መማር ማስተማሩን ውጤታማ ለማድረግ መንግስት የትምህርት ለትውልድ ንቅናቄን ቀርጾ  ደረጃቸዉን የጠበቁ  ትምህርት ተቋማት እንዲኖሩ ለማድረግ  እየሰራ መሆኑን ገልጸው  በባልቻ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የተሰሩ የመማሪያ ክፍሎች ፣ የአይ ሲቲ ክፍሎች ፣ ቤተ ሙከራዎች ፣ ቤተ መጻህፍትና መሠብሰቢያ አዳራሾች  የተሻሉ መሆናቸውን በመግለጽ  የተሰሩ ስራዎች መማር ማስተማሩን በማጠናከር የተማሪዎች ውጤት እንዲሻሻል የሚያግዙ ናቸው ብለዋል።

የትምህርት ቤቱ መምህራን በትርፍ ጊዜያቸው የከተማ ግብርና ስራዎችን እያከናወኑ መሆኑን የገለጹት የቋሚ ኮሚቴው አባላት ተማሪዎች ከትምህርት ጊዜያቸው ጎን ለጎን የተለያዩ ሙያዎችን እንዲማሩ በማድረግ አምራች ዜጋ እንዲሆኑ ስለሚረዳ ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባዋል ብለዋል።

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

https://twitter.com/aacaebc

SITE VISITORS

  • 0
  • 27
  • 222
  • 1,581
  • 6,361
  • 214,622
  • 214,622