በየካቲት 23 ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ምልከታ ተካሄደ ።

by | ዜና

(ቀን ታህሳስ 17/2016 ዓ.ም) በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ በሚገኘው በየካቲት 23  ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ምልከታ ተካሄዳል።

የትምህርት ቤቱን ደረጃ ለማሻሻል በትምህርት ቤቱ የተካሄደውን እድሳት ያለበት ደረጃን አስመልክቶ ምልከታው የተካሄደ ሲሆን  በምልከታው የአዲስ አበባ ብልፅግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ምገስ ባልቻ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር ዘላለም ሙላቱ ፣ የቢሮ አማካሪ አቶ ጥላሁን ፍቃድ ፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የዲዛይንና ግንባታ ስራዎች ቢሮ ሀላፊ ኢንጂነር አያልነሽ ሐብተማሪያም ፣ የክፍለ ከተማው ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አይዳ አወል ፣የክፍለ ከተማው ብልፅግና ፓርቲ ጽ/ቤት ሀላፊ አቶ ሙስጠፋ ትኩና ሌሎች ጉዳዪ የሚመለከታቸው አካላት ተገኝተዋል።

በትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ የትምህርት ተቋሙን ደረጃ ለማሻሻል እንዲቻል በትኩረት መስራት እንደሚገባ በምልከታው ወቅት የተገለፀ ሲሆን በቀጣይ መሰራት በሚገባቸው ጉዳዮች ላይ አቅጣጫ ተቀምጣል።

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 26
  • 222
  • 1,580
  • 6,360
  • 214,621
  • 214,621