በኮልፌ ቀራኒዩ ክፍለ ከተማ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ላይ የመስክ ምልከታ ተካሄደ።

by | ዜና

(አዲስ አበባ ታህሳስ 1/2016 ዓ.ም) በምልከታው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ፣ የቢሮ ማኔጅመንት አባላት ፣ የኮልፌ ቀራኒዩ ክፍለ ከተማ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ንጋቱ ዳኛቸው       እንዲሁም የክፍለ ከተማው ትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ገነነ ዘውዴ  እና  ሌሎች  አመራሮች ተሳታፊ ሆነዋል።

       

አመራሮቹ ምልከታ ያደረጉባቸው ትምህርት ተቋማት  ሰላም በር  1ኛ ደረጃ ፣  ዋቆ ጉቱ  2ኛ ደረጃ  ፣  ካራ ቆሬ ቅድመ አንደኛና መካከለኛ  ደረጃ  ፣ ጋራ ፉሪ አንደኛ  ደረጃ  ፣ ቡርቃ ቡርር  ቅድመ አንደኛና መካከለኛ ደረጃና  አየር ጤና 2ኛ ደረጃ   ትምህርት ቤቶች ናቸው።

       

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ዘላለም ሙላቱ ምልከታ የተደረገባቸው የትምህርት ቤት አመራሮች  ከተማሪና ወላጅ አደረጃጀት ጋር የቅርብ ግንኙነት በመፍጠር በትምህርት ለትውልድ ንቅናቄ የተጀመረውን የትምህርት ተቋማት ደረጃ  የማሻሻል ሰራ ውጤታማ እንዲሆን በትኩረት እንዲሰሩ አቅጣጫ ሰጠዋል። በተጨማሪም  የክፍለ ከተማና የወረዳ አመራሮች ለትምህርት ተቋማት  የሚያደርጉትን ድጋፍና ክትትል አጠናክረው መቀጠል እንደሚገባቸው አስገንዝበዋል።

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 27
  • 222
  • 1,581
  • 6,361
  • 214,622
  • 214,622