በከተማ አስተዳደሩ በሚገኙ የመንግስትና የግል ትምህርት ተቋማት ሱፐር ቪዥን ለሚያካሂዱ የኢንስፔክሽን ባለሙያዎችና ሱፐርቫይዘሮች ኦረንቴሽን ተሰጠ፡፡

by | ዜና

አዲስ አበባ ነሀሴ 23 /2015 ዓ.ም ሱፐርቪዥኑ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ስር ከሚገኙ መዋቅሮች የተውጣጡ ሱፐርቫይዘሮችና በአዲስ አበባ ከተማ የትምህርት ጥራትና ቁጥጥር ባለስልጣን ስር ከሚገኙ ቅርንጫፎች የተውጣጡ የኢንስፔክሽን ባለሙያዎች የሚካሄድ ሲሆን ከሁለቱም ተቋማት የተውጣጡ 490 የሚሆኑ ባለሙያዎች የተቋማቱን የ2016 ዓ.ም ቅድመ ዝግጅት ምልከታ እንደሚያደርጉ ተገልጻል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ ምክትል ቢሮ ኃላፊ አቶ አሊ ከማል በመርሀ-ግብሩ ባስተላለፉት መልዕክት በከተማ አስተዳደሩ የሚገኙ የመንግስትም ሆኑ የግል ተቋማት ወጥ በሆነ መልኩ ተመሳሳይ ስርዓተ ትምህርት ተግባራዊ ማድረግ ስለሚገባቸው ስርዓተ ትምህርቱ በአግባቡ ተግባራዊ መሆኑን ጥብቅ በሆነ የድጋፍና ክትትል ስራ መከታተል ስለሚገባ ሱፐርቪዝኑን ማካሄድ ማስፈለጉን ጠቁመው ተቋማቱ ለ2016 ዓ.ም ያደረጉትን ቅድመ ዝግጅት በቼክ ሊስቱ መሰረት በማየት ትክክለኛ መረጃን መሰረት ያደረገ ግብረመልስ ማቅረብ እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ የትምህርት ጥራትና ቁጥጥር ባለስልጣን ምክትል ስራስካሄጅ አቶ አድማሱ ደቻሳ በበኩላቸው ሁለቱ ተቋማት በቅንጅት በመሆን በአንዳንድ የግል ትምህርት ቤቶች የሚስተዋሉ የስርዓተ ትምህርት ጥሰቶችን ለመቅረፍ የተለያዩ ተግባራትን በማከናወን ላይ እንደሚገኙ ጠቁመው ሱፐርቪዝኑ በዋናነት በመንግስት ትምህርት ቤቶች ትምህርት ለትውልድ በሚል መሪቃል የተጀመረው ንቅናቄ በትምህርትቤቶቹ ደረጃ ላይ ያመጣውን መሻሻል እና የግል ትምህርት ቤቶች ለአዲሱ ትምህርት አመት ተገቢውን የእውቅና ፍቃድ መያዛቸውን ማየት የቼክሊስቱ አካል መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

0 Comments

Submit a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *

SITE VISITORS

  • 0
  • 0
  • 175
  • 2,114
  • 9,135
  • 234,185
  • 234,185